አንቀፀ ብርሃን ድንግል ማርያም ሰማያዊ ዙፋን የመድኃኔዓለም/2/ ሰማይና ምድር የማይችሉትን ኸረ እንደምን ቻልሽው ፍህም መለኮትን/2/ የእሳት መጋረጃ ወዴት ተጋረደ ልኡል በጥበቡ ካንቺ ተዋሐደ/2/ የኪሩቤል አምሳል እመብርሃን ናት ሰማያዊ ንጉሥ የከተመባት የመለኮት ዙፋን ድንግል በመሆን ሚካኤል ገብርኤል ሰግደው ዘመሩልሽ ሩፋኤል ራጉኤል ሰግደው ዘመሩልሽ