ወደ ምሥራቅ እዩ ወደ ፀሐይ መውጫ ድንግልን ክበቧት እንበል ሃሌ ሉያ ለአምላክ እናት ለአዛኝት /2/ እልል እንበል እንዘምርላት /፪/ ወገኖች ተነሡ እናችን መጣች ስሟን ስንጠራ መኟ ትቀራለች የተከዘን ልጽናና ነይ ሰንላት ትመጣለችና /፪/ የጽጌው ማኅሌት በጸሎት ሲጀመር ማርያም ትመጣለች በደመና አየር ንዒ ስንል በሠዓት ልትባርከን ትመጣለች በእውነት /2/ አዝ ---------------- ፍልሰታ ሲጀመር ቃል ኪዳን ገብታለች የሌሊት ውዳሴን ንዒን ትሰማለች ሕጻናትን በበረከት ልትጎበኝ ትመጣለች በእውነት /2/ አዝ ---------------- በፍጹም ቸርነት እንዲምረን ጌታ በአማላጅነትሽ ሁኚልን መከታ እናችን አለኝችን እንድናለን ድንግል አንቺን ይዘን /2/ አዝ ---------------- ሃሌ ሃሌ ሉያ /2/ እስመ ዝንቱ ዑራኤል እስመ ዝንቱ ለዓለም ብርሃን /2/