ትምክህቴ መድኃኒቴ አንቺው ነሽ /2 እመብርሃን /4/ ምርኩዛችን ሸክም የከበደኝ ደካም ነኝ እኔ ረዳትም የለኝ ከአንቺ በቀር ለእኔ እመአምላክ ደግፊኝ ቁሚልኝ ከጎኔ እመብርሃን (4) ምርኩዛችን የኃጢአትን ቋጥኝ በጅርባዬ አዝዬ እቀበዛበዛለሁ ተገፎ ጸጋዬ በአንቺ እማጸናለሁ ነፍሴን በእጅሽ ጥዬ ምርኩዝ መሠላሌ ጥላ ከለላዬ እመብርሃን (4) ምርኩዛችን ልዩነሽ እናቴ ማርያም ድንግል ማን አዛኝ እንደአንቺ ግራ ቀኝ ቢባል በአንቺ ላይ አረፋ ልቤ ተረጋጋ የሕይወቴ ተስፋ በአንቺ ተዘረጋ እምብሃን (4) ምርኩዛችን ፍጽሞ አርቂልኝ የእኔን ክፉ ሽታ በሽቱሽ መዓዛ አድይኝ እርካታ የኪሩቤል እክናፍ የነፍሴ ዋስትና ነይ ነይ እመቤቴ መርኩዛችን እምብርሃን (4) ምርኩዛችን ከፍቅርሽ ምስጋና ዝም እንዳልል ድንግል አንደቤቴን ፍቺው ኅሊናዬም ይቁሠል የፍቅርሽ ማእበል ይፍሰስ በሕይወቴ በእቅፍሽ ድርጊኝ እንደልጅነቴ እመብርሃን /4/ ምርኩዛቸን