colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

ጎሥዓ ልብየ

ጎሥዓ ልብየ ቃለ ሠናየ /2/ ወአነ አይድእ ቅዳሴሃ ለማርያም /4/ እኔስ የማርያምን ውዳሴዋን እናገራለሁ እንደ አባቴ ዳዊት በበገና እዘምራለሁ ቀን ከሌሊት ሳልል ለምስጋና እተጋለሁ ምርኩዜ ነሽና እመቤቴ በአንቺ እመካለሁ ኦ እመቤቴ በእውነት እንወድሻለን የእውነተኛ መብልን ክርስቶስን ወለደሽልን ምክንያተ ድኂን ሆይ ድንግል ማርያም የአምላክ መገኛ በአማላጅነትሽ በመታመን እንጮሃለን እኛ ምሕረትን አድይን ኪዳነምሕረት የዓለም መዳኛ ስለቸርነትሽ እመቤቴ ለእኔ እናቴ ነሽ ስለ ንግሥትነትሽም እምቤቴ ነሽ ዝናባት ሳያጠጡት አየራትም ሳያሳድጉት ሰማያዊ እንጀራ የሰጠሸን ቤተልሔማዊት ቃና ዘገሊላ በሠርግ ቤት በዚያ ተገኝተሸ ሳለሽ ውኃውን ወደ ወይን በአንቺ ምልጃ እንዳስለወጥሽ ዛሬም የእኔ ሕይወት ወይኑ አልቆ ባዶ ሆኗልና አንቺ የአምላክ እናት ንጽሕት ቅድስት ርኅርኂተ ኅሊና ሕይወቴን ቀድሰሽ እመቤቴ ሙይው በምስጋና