colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

የጽድቅ በር ነሽ

የጽድቅ በር ነሽ የሙሴ ጽላት አክሊለ ሰማእታት ምእራገ ጸሎት የጌታዬ እናት ንጹሕ አክሊላችን ሐመልማለ ሲና እመቤታችን /2 እመቤታቸን ለእኛ መርኩዝ ነሽ ከለላም ሆንሽ የእሳት ሙዳይ እሳት ታቀፍሽ በብርሃን ተከበሽ ወርቅ ለብሰሽ ከሴቶች ሁሉ አብ መረጠሸ እመቤታቻን ድንግል ሆይ ልጆችሽ ዘወትር ይጠሩሻል ስምሽን ለልጅ ልጅ ያሳስቡልሻል በተሰጠሸ ጸጋ በአማላጅነትሽ ምሕረትን አሰጪን ከመሐሪው ልጅሽ እመቤታችን ያልታረሰች እርሻ ዘር ያልተዘራባት የሕይወትን ፍሬ ሰጠችን የእኛ እናት የተሠዋው መሲህ እናቱን ወደዳት በቀኙ ቆማለች ድንግል እመቤት ናት እመቤታችን የእውነት ደመና ዝናብ የታየባት ወዳናለች ድንግል የታተመች ገነት ክብር ለሆነችው ኑ እንዘመርላት ደስ ይበልሽ እንበል ለብርሃን እናት