ለማርያም ደንግል መንበረ ተድላ (2) ወሪዶ ገብርኤል ምደረ ገሊላ ትወልዲ ወልድ ለድንግል ይቤላ አዲስ ዜና ለማርያም ድንግል ሰማያት ሠንጥቆ መጣ ገብርኤል ድንግል ከአንቺ ጋር አምላክ ስለሆነ ምክንያት አንቺ ሆነሽ ዓለም ሁሉ ዳነ መዝገበ ጽድቅ ነሽ ምስጋና ይገባሻል ሰማያዊ ጌታ ድንግል ሆይ ወልደሻል መመኪያ ሞገስ ለእኛ ልትሆኝን በስለት ወለዱሽ ሐናና ኢያቄም በማይደክም ልሳን በመላእክት ዜማ ትመሰገናለች የእኛ እናት በራማ ጌታችን ተፀንሶ በማኅፀኗ ሳለ የመላእክት ዝማሬ ትሠማ ነበር የነቢያት ትንቢት ፍጻሜ አገኘ ገብርኤል ተልኮ መድኃኒት ተገኘ ንጹሕ ዘር ከሆነች ከእመቤታችን በፍቃዱ ወርዶ ተወለደልን