colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

ደስ ይበልሽ

ደስ ይበልሽ(2) ማርያም ንጽሕት ድንግል ደስ ይበልሽ ከሴቶቹ ሁሉ የተባረክሽ ነሽ(2) ሰላም እልሻለሁ ማርያም ድንግል እንደ ብሥራታዊው እንደ ገብርኤል ላንቺ የተሰጠሽ ሁለት ድንግልና አንደኛው በሥጋ ሌላው በኅሊና አዝ ከዓለም ሁሉ ሴቶች ንጽሕት በመሆንሽ ሰማያዊው ምሥጢር የተገለጸብሽ የልዑል ማደርያ ለመሆን የበቃሽ የጌታችን እናት በጣም ደስ ይበልሽ አዝ የተነበየላት ሕዝቅኤል ነቢይ የተዘጋችው በር ብሎ በራዕይ ሳይከፍት ገብቶ ወጣ የእስራኤል ጌታ ደግሞ ለዘላለም ትኖራለች ተዘግታ አዝ ማርያም ስትጎበኛት ወደ ቤቷ ገብታ ኤልሳቤጥ ዘመረች በመንፈስ ተሞልታ በማኅፀኗ ያለው ዘለለ በደስታ እኛንም ትጎብኘን ከጠዋት እስከማታ አዝ