በምን በምን እንመስላት ድንግል ማርያምን/2/ ምሳሌ የላትም የላትም ክብሯን የሚመጥን/2 የሙሴ ጸላት ነሽ የምሕረት ቃል ኪዳን የያእቆብ መሠላል የአብርሃም ድንኳን የብርሃን መውጫ የኖኅ ድንቅ መርከብ የመላእክት እህት የሩኅሩኀን ርግብ /2/ በምን በምን እንመስላት ድንግል ማርያምን/2/ ምሳሌ የላትም የላትም ክብሯን የሚመጥን/2 የሰሎሞን አክሊል የአሮን በትር የእዝራ መስንቆ የጌዴዎን ፀምር ድንግል እመቤት ናት የጻድቃን በር ሆና የታገኘች የአምላክ ማኅደር/2 በምን በምን እንመስላት ድንግል ማርያምን/2/ ምሳሌ የላትም የላትም ክብሯን የሚመጥን/2 የቅዱሳን እናት የዓለም ንግሥት ችላ ተሸከመች በሁለት እጇ ይዛ ብርሃን ትሁነን ጨለማን ገላልጣ አማልዳ ታስምረን ከዚህ ዓለም ጣጣ/2/ በምን በምን እንመስላት ድንግል ማርያምን/2/ ምሳሌ የላትም የላትም ክብሯን የሚመጥን/2 ከማር ይጣፍጣል የድንግል መዓዛ አምላክን አቅፋለች በሁለት እጃእ የዛ ዓለም ሁሉ የዳነው በልጅሽ ነውና እናታችን ጽዮን ይድረስሽ ምስጋና /2 በምን በምን እንመስላት ድንግል ማርያምን/2/ ምሳሌ የላትም የላትም ክብሯን የሚመጥን/2