ድንግል እመቤቴ የሕይወቴ ረዳት የኑሮዬ ጣእም ዋልታ መሠረት እለምንሻለሁ/2/ ፍጹም በረከት/2/ ትኅትናሽ ሲታሰብ ድንግል እመቤቴ በሰዎች ልቡና ድንግል እመቤቴ ግርምትን ይፈጥራል ልብ ይመስጥና ጽዮን መጠጊያ ነሽ የአብርሃም ድንኳን የታጠረች ተክል እመብዙኃን ከሚካኤል ጋር ድንግል እመቤቴ ፈጥነሽ ደርሺልኝ ቅዱስ ገብርኤል ይምጣ ክበርሽን ያብስረን ከድንግል ጋር ሆነህ ኡራኤል ፈጥነህ ና ሩፋኤል፤ ራጉኤል ንኡ በደመና በደማችን ሰርጻእል ፍቅሯ የማርያም ምስክር ነን እኛ እስከዘለዓለም በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ስላለን ስምሽን ለልጅ ልጅ እንዘክራለን