ሠላም ለኪ እምነ ጽዮን ማርያም ቅድስት የሕይወት ብርሃን ሰላም ለኪ እምነ ጽዮን ሰላም ልበልሽ ተንበርክኬ በንጽሕናሽ ተማርኬ መርከብ የኖኅ አዳራሽ ሰላም ለኪ ልበልሽ ድንግል የአብርሃም ድንኳን ሰላም /2/ ሐረገ ወይን ያእቆብ ያየሽ መሰላል የሰሎሞን ክብር አክሊል ጽላተ ሙሴ የኦሪት የአሮን በትር መድኃኒት የኖኅ ርግብ የኢያቄም የነቢያት ተስፋ የአዳም እሳተ መለኮትን ያየዝሽ ልኡል አምላክን የወሰንሽ ቤተ መቅደስ የልኡል ሰላም ለኪ እም ወድንግል