የጌታዬ እናት ጸለየች ማርያምም እንዲህ እያለች/2/ ነፍሴ ጌታዬን ታከብረዋለች መንፈሴም በአምላኬ ሐሴት ታደርጋለች የእኔን የባሪያውን ትኅትና የእስራኤል አምላክ ተመልክቷልና/2/ ትውልድ ሁሉ ብፅእት ይሉኛል እርሱ ታላቅ ሥራ አድርጎልኛል ስሙም ቅዱስ ነው ምሕረቱም ለትውልድ ትውልድ ለዘለዓለም/2/ ኃይልን አድርጓል ጌታ በክንዱ ትእቢተኞች ተዋረዱ ገዢዎች ከዙፋን ስለተጣሉ ትሁታን ደግሞ ከፍ ከፍ አሉ/2/ ባለጠጎችም ሲያጡ ሲራቡ ድሆች በምሕረት ጥቂት ጠገቡ ለአባቶቻችን እንደማለ ምሕረቱን አስቦ እኛን ተቀበለ/2/