በሄድኩበት ሂጂ እመቤቴ ይቀናል መንገዴ ኑሮዬም ይሠምራል እመቤቴ አንቺን በመውደዴ በያሬድ ውብ ዜማ እመቤቴ ሁሌ እጠራሻለው በማለዳ ቆሜ እመቤቴ እለምንሻለሁ ቃል ኪዳን ግቢልኝ እመ እግዚአብሔር /2/ የዋኅ ልብሽ ይርዳኝ ከአንቺ ጋር ልኑር ፈጥነሽ ወደ ነይ እመቤቴ ከሰማይ ዳርቻ ምሥጢሬን ሰሚ ነሽ እመቤቴ ድንግል አንቺ ብቻ ሥላሴ የሠሩሽ እመቤቴ የማትፈርሺ መቅደስ ሁሌ ጠዋት ማታ እመቤቴ አንቺን ላወድስሽ ከምድር ብልጽግና እመቤቴ አንቺን እመርጣለሁ ፍቅርሽን ልቀበል እመቤቴ ልቤን እስጣለሁ እንቁ ስምሽ ለእኔ እመቤቴ ክብሬነው እላለሁ እመቤቴ ብዬ እመቤቴ ችግሬን አልፋለሁ ስምሽ ወለላ ነው እመቤቴ ከማር ይጣፍጣል ከጥበባት ሁሉ እመቤቴ እጅግ ይደነቃል ይታተም ምስጋናሽ እመቤቴ በሁለመናዬ ሰአሊ ለነ ልበል እመቤቴ እንዲረዝም እድሜዬ