እሴብሕ ጸጋኪ አምላክነ ዘወለደኪ/2/ ንጉሥነ ዘወለድኪ ውዳሴ ወግናይ አሥርቱ ቃላት ቀድሞ ናት ድንግል ንጽሕት በእውነት አዝ ---- ገብርኤል በቃሉ እያጫወታት ዘኮንኪ ይሏታል ጽርሐ ቅድስት አዝ ------- ናስተማስለኪ ተቅዋመ ማኅቶት አንቺ እግዝእተ ኩሉ የሁሉ እመቤት አዝ ------ ናስተማስለኪ በእፀ ገነት በትረ አሮን ጣትዋ የምትፈትልበት አዝ ----- ለኪ ይደሉ እያሉ መቅደስ አስገቧት መላእክት ወረዱ ሊያመሰግንዋት አዝ ------ በመቅደስ እንድትኖር ስትሰጥ ብጽዓት ዘካርያስ ነበር ሊቀ ካህናት አዝ ----- ወሬ ሆኖ ቀረ የምቀኞች አድማ ሆናለች እሷማ የልኡል ከተማ አዝ -----