በዝናበ ንጽሕኪ ሐረገወይን ፀገየ /2/ ወሮማን /2/ወሮማን ሐዋዘ ፈረየ/2/ እመቤቴ ማርያም ሆይ አንቺን የማይበት/2/ ምን ዓይን አለኝ /5/ ፍቅርሽ አይለየኝ/2/ ለአዳም ተስፋ የሆንሽው ማርያም እመቤቴ /2/ አማልጅን ቶሎ ብለሽ/3/ ሻልጠፋብሽ ልጅሽ /2/ የዳዊት መሰንቆ ነሽ የኢያሱ ሐውልት በምን እንመስልሽ /3/ ወደርም የለሽ /2/ እመቤቴ ጥላዬ ሁኚልኝ ከለላዬ /2 ያለአንቺ ማን አለኝ /3/ አለሁሽ በይኝ /2/ አዳምና ሔዋን ከገነት ተሰደው/2/ ማርያም አንቺ ነሽ/3/ የመዳን ተስፋቸው የእግዚአብሔር አብ ሙሽራ ወልድን የወለድሽ የእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ንጽሕት አዳራሽ የሰሎሞን አክሊል የታጠረች ተክል የአሮን ካህን ልብስ/3/ የወርቅ ጸናጽል