አንደ ኤልሳቤጥ ለመስግንሽ ፊትሽ ወድቄ ልሳለምሽ የጌታዬ እናት የእኛ እመቤት አዛኝ ነሽ ከልብ ፍጹም የዋህት ርኅራኄሽ ያስደስተኛል ስለ ኃጢአቴ ምልጃሽ ይቀድማል የሰላምታሽ ድምፅ ደስ ያሰኘኛል ከትካዜዬም ያሳርፈኛል ድምጽሽ ሲሰማኝ ልቤ ይረካል ሐዘኔ ቀርቶ ፊቴ ይፈካል በእናትነት አንቺን ለሰጠን ቸሩ አምላካችን ይከበር ይመሰገን የሁሉ እቤት የሁሉ አጽናኝ የዓለም መድኃኒት ከአምላክ አገናኝ ዛሬም በልቤ ደስታ ጨምረሽ እንደ ኤልሳቤጥ ሰላም ልበልሽ ከሴቶች መካከል መርጦ ቀድሶሻል ትውልድ ሁሉ ብጽእት ይሉሻል በልዩ ውዳሴ ያመሰግኑሻል ድንግል ንግሥታችን በቀኝ ቆመሻል የሰላምታሽ ድምጽ ልቤ ሲሰማ ነፍሴን ደስ አላት ቀለላት ሽክሟ ድንግል ለክብርሽ ስንበረከክ እጅሽ ይዘርጋ ለመባረክ