ትኅትናሽ ግሩም ነው ደግነትሽም/2/ እናቱ ሆነሻል ለመድኃኔዓለም/2/ ንጽሕት ስለሆንሽ….. እመቤቴ /2/ እንከን የሌለብሽ ……እመቤቴ /2/ የፍጥረታት ጌታ……. እመቤቴ /2/ በአንቺ ያደረብሽ……. እመቤቴ /2/ የድንግል መመረጥ …..አምቤቴ /2/ ዜናው አስገረመኝ……. እመቤቴ /2/ እሳቱን ታቀፈች ……እመቤተ /2/ የማይቻለውን …….. እመቤቴ /2/ ምርኩዜ ልበልሽ…………እመቤቴ/2/ ጥላ ከለላዬ እመቤቴ /2/ ጋሻዬ ነሽ አንቺ እመቤቴ ለእኔ መመኪያዬ በዓለም አንዳልጠፋ እመቤቴ ሕይወቴ መሮብኝ እመቤቴ እንደ ወይን አጣፍጭው እመቤቴ ማርያም ድረሽልኝ እመቤቴ የምሥራቅ ደጃፍ ነሽ እመቤቴ /2/ የሁላችን ደስታ እሙ ለፀሐየ ጽድቅ እመቤቴ የሁሉ ጠበቃ እመቤቴ ድንግል የድል አክሊል እመቤቴ ድንግል የጽድቅ ሥራ ድንግል መሰላል ነሽ እመቤቴ የተዋሕዶ ተስፋ እመቤቴ