ለማርያም/2/ እንዘምራለን ለዘለዓለም/2/ የተዘጋች ደጅ ለዘለዓለም ሕዝቅኤል ብሏል ንጽሕት ናት በእውነት በፍጹም ድንግል አብነት አድርገን እኛም እርሷን ለዘላለም በፍጹም ፍቅር አንዘምራለን /2/ የዋህት ርግብ ለዘለዓለም ሰላም አብሳሪ ለዘለዓለም ጨለማ ሕይወቴ ለዘለዓለም በርሃንን አብሪ ለዘለዓለም እማጸንሻለሁ ለዘለዓለም ድንግል ለነፍሴ ለዘለዓለም አደራ ቅድስት አንቺ ነሽ ዋሴ /2/ እጅግ የበዛ ነው ለዘለዓለም ያለኝ ፍቀር ለዘለዓለም አይወሰንም ለዘለዓለም አይነገርም ለዘለዓለም በእርሷ ደስ ይለኛል ለዘለዓለም ሐሴት አደርጋለሁ ለዘለዓለም ሰሟን እየጠራሁ እዘምራለሁ/2/ ነይ ነይ ስላት ለዘለዓለም ቀንና ሌሊት ለዘለዓለም አትለየኝም ለዘለዓለም ለእኔስ ቅርቤናት እጹብ እጹብ ብለው ለዘለዓለም እመሰገኗት ለዘለዓለም ክብሯን ሊገልጹት ቢያጥራቸው ቃላት /2/