የኖኅ ቃል ኪዳኑ ምልክት ዓርማው የመዳኑ ምሥጢር የሰላም ተስፋው እመቤቴ አንቺ ነሽ ቀስተደመናው/2/ አንቺ የአሮን በትር ሳይተክላእት ያደገች የማክሰኞ እርሻ ያለዘር ያፈራች የሲና ሐመልማል የተዋሕዶ ምሥጢር ክብርት እምቤቴ ሀገረ እግዚአብሔር/2/ የዳዊት መሰንቆ ያሬድ ጽናጽል የደካሞች ምርኩዝ የሰሎምን አኪሊል ሰላሜ ተስፋዬ የሐዘኔ ደራሽ የጽዮን ተራራ መሸሸጊዬ ነሽ/2/ የኤልሳእ ማሠሮ ጨው የተገኘብሽ የሕዝቅኤል ራእይ ንጽሕት አዳራሽ አንቺ የአዳም ተስፋ የመዳኔ ብስራት አንቀጸ ብርሃን የአማኑኤል እናት/2/