ሠላም ለኪ /2/ ለኖኅ ሐመሩ ሠላም ለኪ ለአሮን በትሩ ሠላም ለኪ ለቅዱስ ዳዊት መሰንቆ መዝሙሩ ሠላም ለኪ ለጌዴዎን ፀምሩ ሠላም ለኪ የሰሎሞን መንበረ ክብሩ ሠላም ለኪ ለፍሬ ስብሐት መጾሩ /2 እመ እግዚአብሔር ፀባኦት ሰላም ለኪ/2/ ሠላም ለኪ ሰረገላሁ ለአሚናዳብ ሰላም ለኪ መና ያለብሽ ንጹሕ መሶብ ሰላም ለኪ ያእቆብ ያየሽ በሎዛ የይስሐቅ መዓዛ /2/ እንዘ ንሴፎ ለበረከትኪ ዘምስለ አምኃ ንሰግድ ለኪ/2/ ሠላም ለኪ ኅብስተ መና ዘእስራኤል ሠላም ለኪ የሰማእታት ንጹሕ አክሊል ሠላም እፀ ጳጦስ ዘሲና ሰላም ለኪ የኤልያስ መና እንዘ ንሴፎ ለበረከትኪ ዘምስለ አምኃ ንሰግድ ለኪ /2/