አስታርቂኝ ድንግል ማርያም /2/ ከልጅሽ /3/ ከመድኃኔዓለም አስታርቂኝ ኃጢአትን ሰርቼ አስታርቂኝ ጫካ ውስጥ ቆሜአለው አስታርቂኝ ሥራዬ አሳፍሮኝ አስታርቂኝ ዘወትር አነባለው አስታርቂኝ ልጄ አዳም ብሎ አስታርቂኝ አምላኬ ሲጠራ አስታርቂኝ እነሆኝ ለማለት አስታርቂኝ አንደበቴ ፈራ አዝ ------------ አስታርቂኝ ሀብትን ተካፍዬ አስታርቂኝ ከገዛ አባቴ አስታርቂኝ ከቤቴ ኮበለልኩ አስታርቂኝ ይሻለኛል ብዬ አስታርቂኝ ገፍቼ ወጥቼ አስታርቂኝ የቤቴን ገበታ አስታርቂኝ ልበላ ተመኘሁ አስታርቂኝ የእንስሳት ገፈራ አዝ--------- አስታርቂኝ ወደ አባቴ ልሂድ አስታርቂኝ አሁን ተነሥቼ አስታርቂኝ ይቅርታ ልጠይቅ አስታርቂኝ እግሩ ስር ወድቄ አስታርቂኝ ልጅነቴ ቀርቶ አስታርቂኝ አድርገኝ ባርያህ አስታርቂኝ ከሞያተኞችህ አስታርቂኝ እንደ አንዱ ቆጥረህ አዝ ------ አስታርቂኝ ገና ሩቅ ሳለው አስታርቂኝ አባቴ አይቶኝ አስታርቂኝ ወደእኔ ሮጦ አስታርቂኝ አቅፎ ነው የሳመኝ አስታርቂኝ ጠፍቶ የነበረው አስታርቂኝ ተገኘልኝ አለ አስታርቂኝ ሞቶ የነበረው አስታርቂኝ ደግሞ ሕያው ሆነ