ደስ ይበለን በጣም ደስ ይበለን/2/ በረከቱን ለኛ ስለሰጠን በጨለማ ስኖር ደስ ይበለን በኃጢአት ተከበን የሕይወትን ብርሃን ጽድቁን አበራልን ወደ ምሥራቅ እንይ ፀሐይ ወደአለበት ጨለማው ልባችን ጎህ እንዲገባበት አዝ ------------ የፀሐይ እናቱ ደስ ይበለን ማርያም እመቤቴ እለምንሻለሁ እስከ እለተሞቴ የልቤ ማረፊያ የዘለዓለም ቤቴ አንቺ ነሸ ተስፋዬ እፀ መድኃኒቴ አዝ ---------- የግሽኗ ንግሥት ደስ ይበለን የአምላክ እናት ሆና ተገኝታለች ለሚመኩባት በልቼ ጠጥቼ የምረካብሽ ጎጆ ማረፊያ ማርያም አንቺ ነሽ አዝ ---------- ፀዓዳ እመቤቴ ደስ ይበልን ሐመልማለ ሲና ደስ ይበለን የሕዝቅኤል ደጃፍ የሙሴ ደመና የተዋበች እንቁ የደጎች አዝመራ በማኅፀንሽ ፍሬ ሕይወታችን በራ