ለምኚ ድንግል ለምኚ /2/ ለኃጥአን /3/ አይደለም ለጻድቃን /፪/ ለምኚ ታላቅ ስጦታዬ ለምኚ አዛኝ ሩኅሩኅ ነሽ ለምኚ የጌታዬ እናት ለምኚ ጸጋን የተሞላሽ ለምኚ የአምላክ ማደሪያ ለምኚ ለምነሽ አስምሪን ለምኚ አማናዊት ጽዮን ለምኚ ከእኛ አትለይኝ አዝ-------------- ለምኚ ሐዘንሽ አዘኜ ለምኚ ለእኔ ይሁን ድንግል ለምኚ የተንከራተትሽው ለምኚ በሀገረ እስራኤል ለምኚ ትእግሥትሽን ሳየው ለምኚ ልቤ ይመሰጣል ለምኚ የሐዘን እንባ ጎርፍ ለምኚ ዓይኔን ይሞላዋል አዝ------------------ ለምኚ በቀራንዮ አምባ ለምኚ በዚያ የፍቅር ቦታ ለምኚ በእግረ መስቀሉ ሥር ለምኚ ከክርስቶስ ጌታ ለምኚ ለእኛ ተሰጥተሻል ለምኚ እናት እንድትሆኝን ለምኚ ልጆችሽ ነንና ለምኚ ምልጃሽ አይለየን አዝ---------- ለምኚ አንደበቴን ጌታ ለምኚ በምስጋና ምላው ለምኚ ደስ ይበልሽ ብዬ ለምኚ እኔም ላመስግናት ለምኚ አንደበቴን ጌታ ለምኚ በምስጋና ምላው ለምኚ ደስ ይበልሽ ብዬ ለምኚ እኔም ላመስግናት አዝ----------