ባክኛለሁና በሥጋ ፈተና የዚህ ዓለም ሐዘን ጫፍ የለውምና ፈጥነሽ ወደ እኔ ነይ ከትንሻእ ቤቴ አጽናኚኝ እመአምላክ ድንግል እመቤቴ ባሕሩ ትልቅ ነው ድንግል እመቤቴ ትንሽ ናት መርከቤ /2/ ድንግል እመቤቴ የመንገዴ መሪ ድንግል እመቤቴ አንቺ ነሽ ወደቤ /2/ ድንግል እመቤቴ በመንገዴ ብዝል ድንግል እመቤቴ ዓለም ትስቃለች /2/ድንግል እመቤቴ መመኪያ እመቤቱ ድንግል እመቤቴ ወደየት ናት እያለች /2/ድንግል እመቤቴ በቀቢጸ ተስፋ ድንግል እመቤቴ እንዳልወደልቅብሽ ድንግል እመቤቴ በቀንም በሌሊት ድንግል እመቤቴ ተስፋዬ አንቺ ነሽ ድንግል እመቤቴ የለም ያተረፍኩት ድንግል እመቤቴ ወጥቼ ወርጄ /2/ ድንግል እመቤቴ ትርፌ አንቺ ብቻ ነሽ ድንግል እመቤቴ ጽዮን አማላጄ ድንግል እመቤቴ