ለውሳሴሽ ልትጋ ስምሽ ግርማ ያለው/2/ እመቤቴ ኸኸ እመቤቴ ስልሽ እውላለሁ ከልቤ አቀርባለሁ ምስጋና ለስምሽ መለመኛዬ ነው ጽኑእ ቃል ኪዳንሽ በሰላምታ ድምጽሽ ያልጸና ማን አለ ጽንሱ በማኅፀን በደስታ ዘለለ ማርና ወተት ነው የስምሽ ስያሜ እመቤቴ ስልሽ ይቀላል ሽክሜ ቅኔ ማኀሌቴ ሰዓታት መዝሙሩ ያመሰግኑሻል ምድርና ጠፈሩ እናቱ ነሽና አንቺ ለአዶናይ ማለድኩኝ ከፊትሽ ይቅርታውን እንዳይ ሰአሊነ ብዬ ይኸው ተምሬአለሁ በአንቺ ተደግፌ ነገም እኖራለሁ ነይ ነይ እልሻለሁ አንደ ካህናቱ በሰዓታት ጸሎት ቆሜ በሌሊቱ ዝም አልልም እኔ አወድስሻለሁ የዓለምን መከራ እረሳብሻለሁ