በሐዘኔ በጭንቀቴ መጽናኛዬ ነሽ ረዳቴ እመአምላክ አደራ ድንግል እመቤቴ /2/ ለዓለም ተዘርግቶ እጄ ባዶ ሆናል የራሴ ላይ አክሊል ተሸቀንጥሮ ወድቋል ከኤልዛቤል ሸሽቼ መጣሁኝ ወደአንቺ የጎሰቆልኩትን እኔን ተመልከቺ የእግሬ መሰናልክ ለዓለም ደስታ ነው ተስፋ ቢስ መሆኔ ለጠላቴ ድል ነው የደስታ መመንጫ የኤሳቤጥ ዘመድ አንዳልሠናከል ምሪኝ በመንገድ ምድር ትለኛለች ተስፋ ቢስ ብቸኛ ሳለቅስ ሳነባ አይታናለችና ከቤተ መቅደሱ ለእኔ ዘመድ አለኝ በሐዘኔ ሰዓት አይዞህ የምትለኝ ከአመድ የወደቀ ትንሽ ገንዘብ አለሽ ልብሽ ራርቶልኝ ፈልጊኝ አጥብቀሽ እምነቴ እንዳይደክም እንዳልጠፋ ልጅሽ አድጌአለሁና ከደጀ ሰላምሽ