ማርያም /2/ በሉ የተጨነቃችሁ ያዘናችሁ ሁሉ ቅድስት ማርያምን አዘኝቷን ጥሩ የጌታዬ እናትን አዛኝቷን ጥሩ ነይ በሏት ትመጣለች /2/ ሐዘን ጭንቀት ትገላግላለች ደንግል ማርያም ፀምረ ጌድዬን የታቦት ተራራ ደንግል ማርያም የአባ ጊዮርጊስ ደንግል ማርያም የአርጋኖን ሙሽራ ደንግል ማርያም በአዛኝነትሽ ደንግል ማርያም ስንቅ የሆንሽኝ ደንግል ማርያም ዛሬም ፈጥነሽ ስሚኝ ድንግል ማርያም ድንግል አትርሺኝ ደንግል ማርያም ድንግል ማርያም ብሥራተ ገብርኤል የሚካኤል ፋና ደንግል ማርያም አክሊለ ጊዮርጊስ ደንግል ማርያም የሱራፊል ፋና ደንግል ማርያም ነይ ፈጥነሽ ደረሺ ደንግል ማርያም ተጨንቀናልና ደንግል ማርያም ድንግል ማርያም ፍጥረታት በሙሉ ያመሰግኑሻል ደንግል ማርያም የሕይወታችን በር ደንግል ማርያም ድንግል ናት ይሉሻል ደንግል ማርያም እኛ እንጠራሻለን ደንግል ማርያም ሲጨንቀን ሲጠበን ደንግል ማርያም ለአንቺ ልጆች አድርጎ ደንግል ማርያም ጌታ ስለሰጠን ደንግል ማርያም