እስኪ ላግንሽ እመቤቴ ማርያም እስቲ ላድንቅሽ ንጽሕት ቅድስት ማርያም መመኪያ ርስቴ ነሽና እናቴ /2/ አዝ------------------------ አዛኝት ማርያም ክብርሽ ልዩ ነው ለተቸገረ ስምሽ ስንቅ ነው መደኃኒቴ ነሽ እጠራሻለው ከእግርሽ ወድቄ እሰግድልሻለው አዝ --------------------- የኤዶም ወንዝ የገናት ፈሳሽ ምክንያተ ድኅነት ሰው የዳነብሽ ንጹሑን በግ ጌታን ያስገኘሽ አብርሃም ያየሽ እፀ ሣቤቅ ነሽ አዝ ---------- እያሽበሽብኩ ልዘምርልሽ ልዝረፍ ቅኔውን ነይ ላወድስሽ የቅዱስ ጊዮርጊስ ምስጋና አንቺ ነሽ ዳዊት በመዝሙር የዘመረልሽ አዝ ------- አእላፍ መላእክት ዙሪያሽን ከበው ሲያመሰግኑሽ በሰማይ ያየው እፁብ ድንቅ ነው ግሩም ተአምር ዘርዝሬ አልጨርስ ያንቺን ክብር አዝ---------