ናርዶስ ቀጺመታት አሉ በልብሶችሽ መሀል/2/ የገነት ሽቱ ነሽ/2/2/ ማርያም ድንግል የከበርሽ ነሽ አንቺ ከፍጥረት መዓዛሽን ወድዷል ጌታ ፀባኦት ጠላት እንዳይከሠኝ ከጎኔ ሁኝና ነውሬን ሽፍኝው እናቴ ነሽና አዝ --------------- ገሊላዊት ድንግል የገነት ፈሣሽ የቆሠለችውን ሕይወቴን ፈውሽ ሰአሊ ለነ ቅድስት በቀን በሌሊት ለአፌ ጥበብ ነሽ ቅኔ ማኅሌት አዝ ----- ሁልጊዜ ድኅነትን የምንለምንሽ ለእግዚአብሔር ፊት ሞገስን ያገኘሽ ክርስቲያኖች ሁሉ ተስፋ የሚያደርጉሽ ለዓለም የሚበቃ ምልጃ ቃልኪዳንሽ አዝ ----------------------