ወደጄ ሆይ እነሆ ውብ ነሽ የታተመች ፈሳሽ እንከን የሌለሽ የተዘጋች መቅደስ ንጹሕ አዳራሽ ሕዝቅኤል ያየሽ የምሥራቋ በር ማንም ያልገባባት ከአምላክ በስተቀር የልኡል ማደሪያው አማናዊት መቅደስ ስለንጽሕናሽ ምስጋናን እናቅርብ አዝ ---- ሁለቱንም የሆንሽ እናትና ድንግል ማኀደረ መለኮት ወላዲተ ቃል ያለዘርአ ብእሲ በኅቱም ድንግልና አምላክን የወለድሽ ሐመልማለ ሲና አዝ ------ ምሥራቀ ምሥራቃት ድንግል ሆይ አንቺ ነሽ ጨረቃን የምታመስይ ፀሐይን የወለድሽ የማለዳ ብርሃን ለዓይን የምታሣሺ ጽዮን እናቴ ሆይ ከጎኔ አትሺሺ አዝ --------