የሰማይ የምድር የአርያም ንግሥት አንቺ ነሽ እመቤት የአምላክ እናት ኸኸ ድንግል አማልጅኝ ኸኸ ቅድስት ተራጂን የሔዋን ተስፋዋ የአዳም ዘር ሕይወት የድኅነቱ ምክንያት አንቺ ነሽ ንጽሕት የኦሪት መጽናኛ የሐዲስ ኪዳን ብር የወንጌል መሠረት የአምላክ ማኅደር አዝ -------- የአብርሃም ድንኳን የምሥጢር ዋሻው እናትና ድንግል ሁለቱን ሆንሽው የኤፍሬም ውዳሴ የያሬድ ውብ ዜማ የማትጠልቂ ፀሐይ የሃይማኖት ሻማ አዝ --------