በልኡል መጠጊያ የሚኖር በልኡል መጠጊያ/2/ ይከልላል ከክፉ/2/ አንደበቱን ከኃጢአት ከልክሎ አምላኩን ካሰበ ካልተመጻደቀ በሥራው ራሱን ካልካበ ይከለላል ከክፉ/2/ ጨርቄን ማቄን ሳይል ራሱን ለአምላኩ ከሰጠ በዓለም ምደራዊ ሀብት ተታሎ አምላኩን ካልሸጠ ይከለላል ከክፉ /2/ እስከመጨረሻው ለመኖር በእምነቱ ከጸና ካላፈገፈገ ከአምላኩ ሲገጥመው ፈተና ይከለላል ከክፉ/2/