ንጽሕተ ንጹሐን ከዊና ከመታቦት ዘዶር ዘሲና ውስተ ቤተ መቅደስ ነበረት በድንግልና ነበረት/2/ ሲሳያ ኅብሰተ መና ወስቴሃኒ ስቴ ጽሙና 2/ ከንጹሐን ይልቅ ንጹሕ ሆና እንደ ሲና ታቦትም ሆና በቤተ መቅደስ ውስጥ ኖረች በድንግልና በቤተ መቅደስ ወስጥ(፪) ምግቧም የሰማይ እንጀራ ኅብስተ መና መጠጧም ሆኖ የጸጥታ መጠጥ (፪)