ማን እንደ እርሱ እንደ እግዚአብሔር ቸርነቱ ብዙ በሰማይ በምድር ሞገድና ነፋስ የሚ ዘዙለት አብርሕት ቀላያት የመሰከሩለት ኅቱም መቃብርን ሳይከፍት የተነሣ ነፍሳትን ያዳነ ከሲዖል አበሳ አዝ --- ፈዋሴ ድውያን ቸርነቱ ብዙ የጸጋ ልብሳቸው ጽድቅን ለታረዙ የተዋረዱትን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ለባልቴቷ ዳኛ ፈራጅ ለድኃ አደግ አዝ --- የጠፋውን አዳም ሊፈልግ የመጣ ከባርነት ዓለም ከጽልመት ያወጣ ብርሃን ዘበአማን ጨለማን ያራቀ ሰውን ከራሱ ጋር ሞቶ ያስታረቀ አዝ --- በመከራ ሳሉ ሕዝቦቹን ያሰበ ሥጋውና ደሙን ቆርሶ የመገበ ከባቴ አበሳ ምሕረቱ የበዛ ጌታችን እርሱ ነው የሁላችን ቤዛ አዝ ---