እመአምላክ ሙሽራ ነሽ ለቃል ማደሪያ ለመሆን የበቃሽ /2/ ኸኸ አሥራ ሁለት ዓመት በቤተመቅደስ የኖርሽ የመመረጥ ጸጋ ከጌ አገኘሽ በአብሣሪው መልአክ እጹብ ድንቅ ዜና ከሰማይ መጣልሽ አቋርጦ ደመና በስድስተኛው ወር ተልኮ ገብርኤል ቤተ መቅደስ ገባ ሊያበሥራት ለድንግል በልዩ ሰላም ሰላም ለኪ ያለሽ የክርስቶስ እናት በጣም ደስ ይበልሽ መላእክት በሰማይ ያመሰግኑሻል ክብር ለአምላክ እናት ይድረሳት ይሉሻል በማ ፀንሸ ቢያድር የሠራዊት ጌ ለመሆን ተመረጥሽ የአምላክ ቅዱስ ቦ የፈጣሪ እናት መሆንሽን ተረድቶ ሰላም ለአንቺ ይሁን አለሽ እጅ ነሥቶ ከፍጡራን ሁሉ አንቺ ትበልጫለሽ ገብርኤል ተልኮ ደስ ን አበሠረሽ ምንኛ ድንቅ ነው ድንግል የአንቺ ብሥራት ጌ ን ትወልጃለሽ የሚል ቃልን መስማት ይሁንልኝ ብለሽ ቃሉን የተቀበልሽ ድንግል ሆይ እናቴ እጅግ ልዩ እኮ ነሽ