ማርያም/3/ ደስ ይበልሽ በገብርኤል ሰላም በአንቺ ስለአደረ የዓለም ሁሉ ጌ /2/ የአምላክ ቸርነቱ ፈቃዱ ሲሆን ጨለማ ተገፎ ሲወጣ ብርሃን አዝ --- መድኃኒት ሲመጣ ሰይጣን እንዳፈረ የዜናው አብሣሪ ገብርኤል ነበረ አዝ --- ድንግል ተቀምጣ በቤተመቅደስ ሐርና ወርቁን አስማም ስትፈትል አዝ --- ገብርኤል /2/ ዜናዊ ሐዲስ የአምላክ መወለድ ሥጋ በመልበስ አዝ - - - ገብርኤል ሲያበስራት ድንግል ስትሰማ በእርሷ ላይ አደረ በመንክር ግርማ አዝ --- እውነተኛ መልአክ መሆኑን ስላየች ይሁንልኝ ብላ ቃሉን ተቀበለች