እመቤቴ ጥላ ከለላዬ ረዳቴ የገነት ሙሽራ /2/ የገነት ሙሽራ /3/ ማርያም የልዑል ማደሪያ መጣ በነቢያት ቃለ አብ ተሰብኮ በስድስተኛው ወር ገብርኤል ተልኮ ቤተመቅደስ ሳለች ሳለች በፍጹም ት ትና ደሽ ይበልሽ አላት መልአኩ መጣና በጥዑም ቃል እርሷን እያጽናና /2/ አዝ --- እኔ ወንድ ሳላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል ብላ ጠየቀችው በትኅትና ቃል ገብርኤልም አላት አትፍሪ ማርያም እግዚአብሔር ፍጹም ነው የሚሳነው የለም /2/ አዝ --- መንፈስ ቅዱስ ቀርቦ ይጸልልሻል የልዑልም ኃይሉ በአንቺ ያድርብሻል ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይሆናል ዘለዓለም ዓለምን የሚዋጅ /2/ አዝ --- ይሁንልኝ ብላ ቃሉን ተቀበለች በፍጹም ተዋሕዶ የአምላክ እናት ሆነች ድንግል ማርያም በእውነት ልዩነች /2/ አዝ ---