ሣር ቅጠሉ ሰርዶው ሰንበሌጥ ቄጠ?ማው በዚያች ወር በዚያች ቀን ለምልሞ የነበረው በእልል ዘመሩ በደስ ተሞልተው ጌ መወለዱን የምሥራች ሰምተው እልል በይ ቤተልሔም ሃሌ ሃሌ ሉያ የፍቅር የሰላም ነሽና ገበያ /2/ ያ ትጉህ እረኛ ሳለ በትጋት ብርሃንን ለበሰ በእኩለ ሌሊት ጥሪ ተደርጎለት ከሰማይ ሠራዊት ለመመልከት በቃ የጌ ውን ልደት አዝ --- የእረኝነት ሥራ ተንቆ እንዲቀር ብሎ ሰው በልማድ ደንግጎ ነበር አምላክ የመረጠው መሆኑን እረኛ ክርስቶስ ሲወለድ ተረዳነው እኛ አዝ --- የተነበዩለት ነቢያት በሙሉ ጌ ተወለደ የምሥራች በሉ ሰውን በመውደዱ ሰማያዊው ንጉሥ ይኸው ተወለደ እኛን ለመቀደስ አዝ --- የሩቅ ምሥራቅ ሰ−ች ሰብአ ሰገል ሰምተው ሊሰግዱለት መጡ በኮከብ ተመርተው ዕጣንና ከርቤ ወርቁንም አመጡ እንደየሥርዓቱ እጅ መንሻ ሰጡ አዝ --- ስለተወለደ መድ ን የእኛ ተስፋ /2/ በደል ተወገደ ኃጢአትም ጠፋ /2/