ዜና

Earlier
የቅዱስ ሲኖዶስን ጉባኤ መጀመር አስመልክቶ ከቅዱስ ፓትርያሪኩ የተሰጠ መግለጫ ግንቦት ፲፯ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም የተወደዳችሁ የድረ ገጻችን ተከታታዮች፣ እንደሚታወቀው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፤ ቅዱስ ፓትርያሪኩ ጠዋት ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና ለጋዜጠኞች የሰጡትን ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ወዓዲ እብለክሙ ለእመ ኀብሩ ክልኤቱ አው ሠለስቱ እምኔክሙ በውስተ ምድር በእንተ ኵሉ ግብር ዘሰአሉ ይትገበር ሎሙ በኀበ አቡየ ዘበሰማያት እስመ ኀበ ሀለዉ ክልኤቱ ወሠለስቱ ጉቡአን በስምየ ህየ እሄሉ አነ ማእከሎሙ፤ ዳግመኛም ከእናንተ ሁለቱ ወየም ሦስቱ በምድር ላይ ስለሚለምኑት ሥራ ሁሉ ቢተባበሩ፣ በሰማያዊ አባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል፤ ሁለቱ ወይም ሦስቱ በስሜ ተሰብስበው ካሉበት፣ እኔ ከዚያ በመካከላቸው እገኛለሁና /ማቴ.፲፰፥፲፱-፳/፡፡ [...]
Wed, May 25, 2016
ዐውደ ርእዩ ለስድስት ተከታታይ ቀናት ለተመልካች ክፍት ኾኖ ይቆያል፡፡ ግንቦት ፲፯ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው በማኅበረ ቅዱሳን የተዘጋጀውና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው አምስተኛው ዙር መንፈሳዊ ዐውደ ርእይ የቤተ ክርስቲያን አባቶች፣ የማኅበሩ ሥራ አመራር አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ እንደዚሁም የዐውደ ርእዩ ተመልካቾች በተገኙበት በዐዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማእከል ዛሬ ረፋድ ላይ በአባቶች ጸሎት ተጀመረ፡፡ በጸሎተ ወንጌሉ የተሰበከው ምስባክ፡- ጥቀ ዐቢይ ግብርከ እግዚኦ ወኵሎ በጥበብ ገበርከ መልዐ ምድረ ዘፈጠርከ፤ አቤቱ ሥራህ እጅግ ታላቅ ነው፡፡ ሁሉን በጥበብ አደረግህ፡፡ የፈጠርኸውም ፍጥረት ምድርን ሞላ፤ /መዝ.፻፫፥፳፬/ የሚለው ትምህርት ሲኾን፣ የተነበበው የወንጌል ክፍልም ሉቃ. ፲፥፳፩-፳፬ ያለው ኃይለ ቃል ነው፡፡ [...]
Wed, May 25, 2016
አፕሊኬሽኑ ለሁሉም ስልኮች በሚኾን መልኩ ተሻሽሎ ቀርቧል፡፡ ትምህርቶችን፣ ጸሎታትን፣ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶችን፣ የየዕለቱን ምንባባትና የአብያተ ክርስቲያናት መረጃዎችን ይዟል፡፡ ግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በሰሜን አሜሪካ ማእከል በእጅ ስልክ አማካይነት ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ስብከቶችን፣ መዝሙራትንና ጸሎታትን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችለው ተዋሕዶ የአይፎን አፕሊኬሽን ተሻሽሎ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገለጠ፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ ማእከል ሙያ አገልግሎትና ዐቅም ግንባታ ክፍል ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መረጃ እንደገለጠው፤ በማእከሉ ታቅፈው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በሞያቸው በሚያገለግሉ አባላት ቀደም ሲል የተዘጋጀው አፕሊኬሽኑ ለምእመናን ሰፊ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ [...]
Tue, May 24, 2016
ግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው ረክብ የሚለው ቃል ተራከበ ተገናኘ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጕሙም ማግኛ፣ መገኛ፣ መገናኛ ማለት ነው፡፡ ርክበ ካህናት ሲልም የካህናት መገኛ፣ መገናኛ፣ ጉባኤ (መሰባሰቢያ)፣ መወያያ፣ ወዘተ ማለት ነው /ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገጽ ፰፴፩/፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ቋንቋ ክህነት የሚለው ቃል ከጵጵስና ጀምሮ እስከ ዲቁና ድረስ ያሉትን መዓርጋት የሚያጠቃልል ስያሜ ሲሆን ካህን (ነጠላ ቍጥር)፣ ካህናት (ብዙ ቍጥር) በአንድ በኩል ቀሳውስትን የሚወክል ሆኖ በሌላ በኩል ደግሞ የጳጳሳት፣ የኤጲስ ቆጶሳት፣ የቀሳውስት፣ የዲያቆናት የጋራ መጠሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ርክበ ካህናት (የካህናት ግንኙነት፣ ጉባኤ፣ ስብሰባ፣ ወዘተ) የቃሉ ትርጕም እንደሚያስረዳው የአባቶች ካህናት ማለትም የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት (የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት) ጉባኤ ማለት ነው፡፡ በዓሉ በየዓመቱ የትንሣኤ በዓል በዋለ በ፳፭ኛው ቀን ሁልጊዜ በዕለተ ረቡዕ ይዋል እንጂ ወሩና የሚውልበት ቀን ግን የበዓላትንና የአጽዋማትን ቀመር ተከትሎ ከፍና ዝቅ ሊል ይችላል፡፡ የአጽዋማትና የበዓላት ቀመር ከመዘጋጀቱ በፊት ማለትም በቅዱስ ድሜጥሮስ አማካኝነት ዐቢይ ጾም ሰኞ፣ ስቅለት ዓርብ፣ ትንሣኤ እሑድ፣ ርክበ ካህናት ረቡዕ፣ ዕርገት ሐሙስ፣ ጰራቅሊጦስ እሑድ እንዲሆን ከመደረጉ በፊት ርክበ ካህናት ግንቦት ፳፩ ቀን ይውል ነበር /መጽሐፈ ግጻዌ ግንቦት ፳፩/፡፡ ከዚህ በኋላ ግን ርክበ ካህናት በዓለ ትንሣኤ በዋለ በ፳፭ኛው ቀን፣ በበዓለ ሃምሳ እኩሌታ በዕለተ ረቡዕ ይዘከራል፡፡ በያዝነው ዓመት በ፳፻፰ ዓ.ም የትንሣኤ በዓል ከተከበረበት ዕለት (ሚያዝያ ፳፫ ቀን) ጀምሮ ብንቈጥር ፳፭ኛው ቀን ግንቦት ፲፯ ቀን ይሆናል፡፡ በመሆኑም የዘንድሮው ርክበ ካህናት ግንቦት ፲፯ ቀን [...]
Tue, May 24, 2016
ግንቦት ፲፭ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው በዕለቱ ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ሕይወት በሚል ርእስ በ፲፱፻፺፮ ዓ.ም ባዘጋጁት መጽሐፋቸው ላይ የዳሰሳ ጥናት ቀርቧል፡፡ ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ በስእለት መልክ ለእግዚአብሔር መሰጠታቸውን እኅታቸው ተናግረዋል፡፡ ወጣቱ ትውልድ የእርሳቸውን ፈለግ ተከትሎ ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ ከቻለ አባ አበራ ሕያው ናቸው እንጂ አልሞቱም ተብሏል፡፡ የሊቀ ገባኤ አባ አበራ በቀለ (ስመ ጥምቀታቸው ኃይለ መስቀል) ሰባተኛ ዓመት የዕረፍት ቀናቸው መታሰቢያ ቤተሰቦቻቸው፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራሮችና አባላት በተገኙበት ግንቦት ፲፩ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በማኅበሩ ሕንፃ ተዘክሯል፡፡ [...]
Mon, May 23, 2016
ቅዱስነታቸው የተለያዩ የሀይማኖት መሪዎችና የመንግስት ባለሥልጣናትን አነጋግረዋል፤ በመምህር ሙሴ ኃይሉ እና በመምህር ዳንኤል ሠይፈ ሚካኤል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትየጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዳግማይ ትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ሐዋርያዊ ጉብኝት አደረጉ፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን አስከትለው ረቡዕ ሚያዝያ 26 ቀን 2008 ዓ.ም ምሽት ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ብዛት ያላቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ከፍተኛ አሸኛኘት ያደረጉላቸው ሲሆን በእስራኤል ቴልአቪቭ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱም በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ክቡር አቶ ህላዌ ዮሴፍ እና የኤምባሲው ሠራተኞች፣ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም፣ የገዳሙ መጋቢ አባ ፍስሐ፣ እና የገዳሙ ማኅበረ መነኮሳት፣ የኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት እና ብዛት ያላቸው ምዕመናን ከፍተኛ መንፈሳዊ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ [...]
Sat, May 21, 2016
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤ በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤ ሞትንና መቃብርን ድል አድርጎ የተነሣው፣ የሕይወት ራስና የሁሉ ፈጣሪ የሆነው፣ ጌታችን፣ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ስምንት ዓመተ ምሕረት በዓለ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ !!‹‹ዓይቴ እንከ ቀኖትከ ሞት፤ ወዓይቴ እንከ መዊዖትከ ሲኦል፤ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ?ሲኦል ሆይ ድል መንሣትህ የት አለ?›› /1ቆሮ. 15፡55/፡፡የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናትሞትና መቃብር የኃጢአትና የበደል ውጤቶች እንጂ የተፈጥሮ ዕድል ፈንታ ሆነው ለሰው የተሰጡ አይደሉም ፡፡ [...]
Sat, Apr 30, 2016
· የ2008 ዓ.ም በዓለ ስቅለት በእመቤታችን ቀን ውሏል። እናም ይሰገዳል? ወይስ አይሰገድም?· ይኸው ገጠመኝ በ1913 ዓ.ም ተከስቶ በነበረበት ወቅት አበው ጉዳዩን እንዴት ፈቱት?(መምህር ጳውሎስ መልክአ ሥላሴ):- በተወሰኑ ዓመታት መካከል የስቅለት ዕለት በየጊዜው ዘንድሮ እንደሆነው ሲገጥም ክርክር ይነሳል። አስታውሳለሁ የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪ ሳለሁ እንዲሁ ስግደት በእመቤታችን ዕለት በመዋሉ ምክንያት በተለያዩ አድባራት ተበታትነን በዓሉን የምናሳልፍ ተማሪዎች እንደየደብሩ አለቃ ስሜት ወይም ግንዛቤ አሳልፈን ተመልሰናል። ማለትም አንዱ ጋር ይሰገዳል አንዱ ጋር አይሰገድም። ይህ ክርክር ዘንድሮም ቀጥሏል። ቅዱስ ሲኖዶስ የማያዳግም ምላሽ ቢሰጥበት መልካም ነው። በቅድሚያ ጾሙን በጥሩ ሁኔታ የቻላችሁትን ያክል በትጋት ላሳለፋችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ድካም ባለው ተጋድሎዋችሁ ቸርነቱን አክሎበት የልባችሁን መሻት ይስጥልኝ። የጾምና ጸሎታችሁም በረከት ይድረሰን ለብርሃነ ትንሳኤውም በሰላም ያድርሰን እላለሁ።ወደ ተነሳሁበት ጉዳይ ስመለስ ዘንድሮ ስቅለት በእመቤታችን ቀን ውሏል። እናም ይሰገዳል? ወይስ አይሰገድም? በሕማማት ውስጥ ከትንሳኤ በፊት ያለችው ቅዳሜ የተሻረች ሰንበት ትባላለች (ቀዳሚት ስዑር) ሃይማኖተ አበው እንደሚያዝዘን በቅዳሜ ቀን መጾም ክልክል ነው። ከቀዳሚት ስዑር በቀር ይላል ስለተሻረች የሕማማትን ቅዳሜ እንጾማታለን በሕማማት ውላለችና። ልክ እንደዚሁ በሕማማት ማንኛውም በዓል ቢውል አይከበርም።የእመቤታችን በዓል ስለሆነ ስግደት የለም ካልንና ካልሰገድን ቅዳሴ ሊኖር ይገባ ነበር። ቅዳሴ ሳይቀደስ የሚከበር የእመቤታችን በዓል የለንምና ስለዚህ የነገው አርብ ይሰገዳል። ይህ የኔ አሳብ አይደለም የአባቶቼ ትምህርት እንጂ። እስቲ የዛሬ ዘጠና [...]
Thu, Apr 28, 2016
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን‹‹ለሐኮ ለሰብእ በአርአያከ ወበአምሳሊከ፤ ሰውን በአርአያህና በአምሳልህ አበጀኸው›› /ዘፍ.1፡26፣ ቅዱ ያሬድ/ ፈጣሬ ፍጥረታት እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር በሦስት ነገሮች ከሌሎች ፍጥረታት የተለየ አድርጎ ፈጥሮታል፤ይኸውም እንደሌሎች ፍጥረታት ይሁን በማለት በቃል - ትእዛዝ ሳይሆን ከምድር አፈር አበጅቶ ፈጥሮታል፣ ይህም ማለትም ፡- በእጁ አከናውኖ፣ አሳምሮና አክብሮ የፈጠረው በመሆኑ፤ ከሌሎች ፍጥረታት በተለየ ሁናቴ በአርአያውና በአምሳሉ የፈጠረው በመሆኑ፣ ከፍጥረታት ሁሉ ለይቶ የሕይወት እስትንፋስን እፍ ያለበት ሕያው ፍጡር በመሆኑ ከሌሎች ፍጥረታት የተለየ ያደርገዋል፡፡ በኃላፊነት ደረጃም ምድርንና በምድር ያሉትን ፍጥረታት ሁሉ እንዲያስተዳድር፣ እንዲያዝና እንዲገዛ ባለሙሉ ሥልጣን ሆኖ በእግዚአብሔር ተሹሞአል፡፡ይህ ሁሉ የሚያመለክተው ሰው በፈጣሪ ዘንድ እጅግ በጣም የተከበረና የተወደደ ፍጡር ከመሆኑም በላይ አርአያ እግዚአብሔር፣ አምሳለ እግዚአብሔር የሆነ ክቡር ፍጥረት መሆኑን ነው ፡፡ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ክብር - ታላቅነት በሚያስተምርበት ጊዜ ‹‹በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል›› ብሎአል፤ /ማቴ.5፡21-22/ጌታችን በዚህ ትምህርቱ የሰው ልጅን መግደል ይቅርና መሳደብና መቆጣት እንደማይቻል አበክሮ አስተምሮአል፤ ሰውን መግደል አርአያ እግዚአብሔርን፣ አምሳለ እግዚአብሔርን ማፍረስ ስለሆነ በፈጣሪ ዘንድ ትልቅ በደል ነው ፡፡ [...]
Sat, Apr 23, 2016
‹‹እመቦ ዘአሕሰመ ቃለ ላዕለ አቡሁ ወእሙ ሞተ ለይሙት፤አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል›› (ዘጸ. 21፤17፣ ማቴ. 15፡3-4) እስክንድር ገብረ ክርስቶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት የባህልና የታሪክ መገኛ በመሆኗ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ጥንተ ሥልጣኔ መሠረት ነች ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የኢትዮጵያ ሕዝብ በመፈቃቀድ፣ በመከባበርና በመቻቻል በአብሮነት ይኖር ዘንድ ሕዝበ ክርስቲያኑን በግብረገብ ትምህርት በማነጽ በልዩነት ውስጥ ላለን አንድነት መጠንከር ታላቅ አስተዋኦን አበርክታለች ፡፡ከአሠርቱ ትእዛዛት አንዱና ‹‹እናትና አባትህን አክብር›› የሚለውን የልዑል እግዚአብሔርን ትእዛዝ መሠረት በማድረግ ሕዝበ ክርስቲያኑ በመከባበር፣ በመደማመጥና በመፈቃቀር ይኖር ዘንድ ለዘመናት አስተምራለች፤ በማስተማርም ላይ ትገኛለች፤ ይህ ትምህርቷም በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘ በመሆኑ በቤተሰብ ደረጃ ሳይቀር ታናሽ ታላቁን እያከበረና በታላቁ እየታዘዘ፣ ታላላቆችም ለወላጆቻቸው እየታዘዙ በመከባበር የሚኖሩበት ሃይማኖታዊ ሥርዓትን ማሥረፅ ችላለች ፡፡ይህ የመከባበርና የመደማመጥ ሥርዓት በቤተ ክርስቲያናችን ደረጃ የጠነከረና የሚያስቀና ሥርዓት ሆኖ ይገኛል ፡፡ ዲያቆናት ካህናትን፣ ካህናት ኤጲስ ቆጶሳትና ሊቃነ ጳጳሳትን፣ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ፓትርያርኩን በማክበር፣ በማድመጥና በመታዘዝ ቤተ ክርስቲያን የሥርዓት ባለቤት መሆኗን በተግባር ለሕዝበ ክርስቲያኑ ስታስተምር ኖራለች፤ አሁንም እያስተማረች ትገኛለች ፡፡በለተይም የሐዋርያት ምሳሌ የሆኑት ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በከፍተኛ ደረጃ ክብር ሊሰጣቸው የሚገቡ አባቶች በመሆናቸው ካህናትና ምእመናን ጉልበታቸውንና መስቀላቸውን ስመው ተገቢውን የሃይማኖት አባትነት ክብር ሰጥተው በሚገባ ያከብሯቸዋል ፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚሰጧቸውን ትእዛዝና መመሪያዎችም ያለማንገራገር ተግባራዊ ያደርጋሉ ፡፡ [...]
Sat, Apr 23, 2016
(ዲባባ ዘለቀ ለደጀ ሰላም እንደጻፉት):- በማኅበረ ቅዱሳን ተዘጋጅቶ “ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ፣ ድርሻችንን እንወቅ” በሚል መሪ ቃል ከመጋቢት 15-21 ቀን 2008 ዓ.ም በኤግዚቢሽን ማእከል ለ5ኛ ጊዜ ሊያካሔደው የነበረው ዐውደ ርእይለእይታ ሊቀርብ ጥቂት ሰዓታት ሲቀር በቀጭን ትእዛዝ ያገደውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዐውደ ርእይ ፀሐዩ መንግሥታችን መፍቀዱን አስታውቋል። “በዚህ ምክንያት ነው ያገድኩት” ለማለት ያልተገደደው የአጼዎቹ መንግሥት ዛሬም እንዲታይ የፈቀደበትን ምክንያት መጠየቅ ነውር ሆኖ ይልቁንም ስለፈቀዳችሁልን "እናንተን ያቆይልን" ለማለት ዳር ዳር እየተባለ ነው። ወያኔ ላለፉት 25 ዓመታት የሕዝብን ተቃውሞ ሲያስተነፍስ የኖረበትም ስልት ይኸው ነው። ለፓለቲካ ዓላማ ወሳኝ የሆኑ ርምጃዎችን በህገ ወጥነትና በድፍረት ይወስድና ሕዝቡ እንዲንጫጫ ካደረገ በኋላ ትንሽ ዘግየት ብሎ ነገሩን የሚያበርድ ከፊል ምላሽ ይሰጣል። ሕዝቡም "ኧረ ይህንንስ እነርሱ ቢሆኑ አይደል? እግዚአብሔር ይስጣቸው!" ብሎ አስቀድሞ የጠየቀውን ጥያቄ ዘንግቶት ዝም ይላል። ይህ ስልት ሳይቀየር ለሩብ ምእተ ዓመት መሥራቱ በራሱ ኢትዮጵያውያን ለማታለል የማናስቸግር “የዋሕ” ሕዝቦች መሆናችንን የሚያረጋገጥ ይመስለኛል። ለምሳሌ በምርጫ ሰሞን የምርጫውን አካሄድ ሊለውጡ ምናልባትም አስቀድሞ የተሰላውን ውጤት ሊለወጡ የሚችሉ ወሳኝ የፓለቲካ መሪዎች፣ ጋዜጠኛች ወይም የሲቪክ ማኅበራት መሪዎች ይታሠራሉ። የታሰሩበት ምክንያት ተጋኖ እና እንኳንስ ሊፈቱ በሞት ለመቀጣት የሚያበቃ ጥፋት እንደተገኘባቸውበጠቅላይሚኒስቴሩ እና በቱባ ባለሥልጣናት ለሀበሻውም ለፈረንጁም ከተነገረ በኋላ (“ብርቱካንን ከምፈታ አዜብን ብፈታ ይቀለኛል ከተባለ በኋላ”) የምርጫው ሒደት ከተጠናቀቀ እና የታሳሪው/ዎቹ ተጽእኖ ፈጣሪነት ከደበዘዘ በኋላ "በምሕረት" ወይም በነጻ በከፊል ይለቀቃል/ሉ። ሐበሻ ሆዬ [...]
Wed, Apr 20, 2016
በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ጊዜው እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ18ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ነበር፡፡ ለአንዳች ተልዕኮ የተነሡ ሞራቪያውያን (የቼክ ሪፐብሊክ ዜጎች የሆኑ) ፕሮቴስታንት ሚስዮናውያን ወደ ግብጽ ገቡ፡፡ ጌታችን ከእናቱ ጋር ወደ ተሰደደባት ፣ በፈጣን ደመና ተጭኖ እየበረረ ወደ ደረሰባት ፣ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ ወዳስተማረባት ሐዋርያዊት የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ‹ጌታን እንሰብካለን› ብለው ዘመቱ፡፡ የእነዚህ ሚስዮናውያን እንቅስቃሴም በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ላይ ላለፉት ሁለት መቶ ዓመታት ሲነድና ሲበርድ ለቆየው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ሴራ መነሻ ነበር፡፡ ሚስዮናውያኑ በሚያምኑበት እምነት ግብጻውያንን [...]
Fri, Apr 15, 2016
የሚከተለው ጽሑፍ በዲ/ን ኤፍሬም እሸቴ ተጽፎ አደባባይ የጡመራ መድረክ (www.adebabay.com) ላይ የወጣ ነው። ደጀ ሰላማውያን ቢያነቡት መልካም ነው በሚል ሐሳብ እነሆ አቅርበነዋል። ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን+++++እንደ ዳራ (Background)(ኤፍሬም እሸቴ/ ephremeshete@gmail.com/ www.adebabay.com)ሁለት የባፕቲስት ሚሲዮን እምነት ተከታዮች የሆኑ ፓስተሮች ባለፈው የጥምቀት ሰሞን አገራችንን መጎብኘታቸውን እንዲሁም ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋርም መነጋገራቸውን በፎቶግራፎች አስደገፈው ያወጡት ዜና ያትታል። ዜናውን በማኅበራዊ ድረ ገጾች ከፍተኛ መነጋገሪያ እንዲሆን ያደረገው የሁለቱ ፓስተሮች ጉብኝት ሳይሆን እንገነባዋለን ያሉት የ50ሺህ አብያተ ጸሎት ጉዳይ እንዲሁም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ናቸው በተባሉት በአፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ላይ (ያውም በፓርላማው መንበራቸው ላይ እንደተሰየሙ) ከዳርና ከዳር ጠምደው ጸሎት ሲያደርጉላቸው የሚያሳየው ፎቶግራፍ ነው። http://www.bpnews.net/46636/layman-plans-for-50000-churches-in-ethiopiaከዚህም ባሻገር የጉዞ ዘገባቸው ያነሣቸው አስገራሚ ነጥቦች አሉ።1ኛ. የጉዞ ወጪያቸውን የሸፈነላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሆኑ፣2ኛ. ከፕሬዚዳንቱ ጀምሮ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ ከመከላከያ ሚኒስትሩ እና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሁም ከአየር መንገድ ኃላፊዎችና በአሜሪካ ከኢትዮጵያ አምባሳደር ጋር መነጋገራቸው እና እነርሱም በሁሉም ነገር እንደሚተባበሯቸው ቃል መግባታቸው መገለጹ፣3ኛ. የተገኙትና ተቃቅፈው ሲጸልዩ ፎቶ የተነሡት በጥምቀት በዓል ላይ ቢሆንም በሌላው ሰው በዓል የራሳቸውን ጸሎት ማድረጋቸው ሳያንስ ለፎቶው የሰጡት መግለጫ እንዲህ ይላል፡- ግርድፍ ትርጉም፡- “የኦርቶዶክስ ክርስትና የጥምቀት በዓል በአዲስ አበባ። ወደ 5 መቶ ሺህ ኢትዮጵያውያን ተካፍለውበታል ይህንን የኢየሱስን ጥምቀት ለማሰብ፤ ነገር ግን በተሳሳተ የነገረ መለኮት ትምህርት የተዘፈቀ … ” ነው። /“… the Christian Orthodox Epiphany festival in Addis Ababa, Ethiopia. About 500,000 Ethiopians attended [...]
Fri, Apr 15, 2016
(አንድ አድርገን መጋቢት 21 2008 ዓ.ም ፡- የምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኝ ሲሆን ይህ ቤ/ክ በ1986 ዓ.ም በአካባቢው ምዕመናን እንደተመሰረተ ይነነገራል፡፡ የቤተክርስቲያኑ ይዞታ ወደ 80ሺ ካሬ የሚጠጋ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ከተሰሩ ወይም በመሰራት ላይ ከሚገኙ እጅግ ግዙፍ ከሚባሉ አብያተክርስቲያናት ውስጥ አንዱ ሊሆን የሚችል ሕንጻ ቤተክርስቲያን እያስገነባ ይገኛል፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር በተለያዩ ስራዎች ለተሰማሩ አስራ ሁለት ግለሰቦች  በወር 157,332 ወርሐዊ ኪራይ የሚያገኝ ሲሆን ከ7ሺህ ካሬ በላይ የሚገኝውን ቦታ ደግሞ   [...]
Wed, Mar 30, 2016