ትምህርት

Earlier
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ድንግልና፡-በሦስት ወገን ነው። በሥጋዋ፥ በነፍሷ እና በልቡናዋ ድንግል ናት፤ ይህ ድንግልና፡- የዘለዓለም ድንግልና ነው። ይህም በምሳሌ ኦሪት፥ በነቢያት ትንቢት የተረጋገጠ ነው። ከአዳም ብቻ በቀር ከድንግል መሬት የተፈጠረ የለም፤ “እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሰው ሆነ፤” ይላል። ዘፍ፡፪፥፯። ከአንድ ከሔዋን ብቻ በቀር ከአዳም ጎን የተፈጠረ የለም፤ “እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ከባድ እንቅልፍን ጣለበት፥ አንቀላፋም፤ ከጎኑም አንዲት አጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው። እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት፤”ይላል። ዘፍ፡፪፥፳፩አበ ብዙኃን አብርሃም፡- ከአንድ በግ ብቻ በቀር ከዕፀ ጳጦስ አላገኘም። “አብርሃምም ዓይኑን አነሣ፥በኋላውም እነሆ አንድ በግ በዱር ውስጥ ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብርሃምም ሄደ፥ በጉንም ወሰደው፥ በልጁም ፈንታ መሥዋዕት አድርጎ ሠዋው፤”ይላል። ዘፍ፡፳፪፥፲፫። አብርሃም የእግዚአብሔር አብ፥ ዕፀ ሳቤቅ የድንግል ማርያም፥ በግ የኢየሱስ ክርስቶስ፥ ይስሐቅ ደግሞ የአዳም ምሳሌዎች ናቸው። አብርሃም፡- ከዕፀ ሳቤቅ የተገኘውን አንድ ብቻ በግ በይስሐቅ ፈንታ እንደሠዋው፥ እግዚአብሔር አብም፡- ከድንግል ማርያም የተወለደውን፥ ለእርሱም ለእናቱም አንድ ብቻ የሆነውን፥ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን፥ ስለ አዳም ልጆች ፈንታ ለሞት አሳልፎ ሰጥቶታል። “እግዚአብሔር አንድ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወድዶአልና። . . . ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም፤” ይላል። ዮሐ፡፫፥፲፯፣ ፩ኛ፡ዮሐ፡፬፥፲።በዚህ ምሳሌ መሠረት፡- [...]
Wed, Feb 17, 2016
ብሥራተ ቅዱስ ገብርኤል፤ብሥራት፡- በቁሙ ሲተረጐም የምሥራች፥ አዲስ ነገር፥ ደስ የሚያሰኝ ወሬ፥ ስብከት፥ ትንቢት፥ ወንጌል ማለት ነው። አብሣሪው፡- “ደስ ይበልህ፥ ደስ ይበልሽ፥ ደስ ይበላችሁ፤” እያለ የተላከበትን እና የመጣበትን የሚናገርበት ነው። ደስ የሚያሰኝ ዜና የተነገረውም አካል፡- “ይሁንልኝ፥ ይደረግልኝ፤” እያለ ብሥራቱን በሃይማኖት ይቀበለዋል። ጥርጥር ከገባው ግን፥ ነገሩ ከእግዚአብሔር በመሆኑ ተግሣጽ ይወድቅበታል። “አባት የሚወደውን ልጁን እንደሚገሥጽ እግዚአብሔርም የሚወደውን ይገሥጻል።” ጻድቁ ካህን ዘካርያስ፡- የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል፡- መጥምቀ መለኰት ቅዱስ ዮሐንስን እንደሚወልድ ባበሠረው ጊዜ፥” እኔ ሽማግሌ ነኝ፥ ምስቴም አርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ?” በማለቱ፥ “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፥ እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር፤ ይህ ነገር እስከሚሆን ቀን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ፤” ብሎታል። ሕፃኑ እስከሚወለድም ድረስ ዲዳ ሆኖአል። ሉቃ፡፩፥፲፰። ቅዱስ ገብርኤል፡- ጥንት በዓለመ መላእክት በሳጥናኤል ምክንያት የተነሣውን ማዕበል ጸጥ ያደረገ መልአክ ነው። ሳጥናኤል፡- ሲፈጠር የመላእክት አለቃ ሆኖ ነው፥ እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ከፈጠረ በኋላ፥ “በሰጠኋቸው አእምሮ ተመራምረው ይወቁኝ፤” ብሎ ተሰወረባቸው። እነርሱም፡- “ከየት መጣን? ማን ፈጠረን?” ማለት ጀመሩ። ይኽንን የሰማ [...]
Tue, Feb 02, 2016
የተጠማ ውሻ፤ውሻ፡- ለበጎም ለክፉም ምሳሌ ይሆናል።በጎ ምሳሌነቱ፡- ለጌታው ታማኝ መሆኑ ነው፥ አስተማማኝ የቤት ጠባቂ ነው። ዘጸ፡፲፩፥፯፣ ኢሳ፡፶፮፥፲። እንደሚታወቀው የሚኖረው በቤት ውስጥ ከሰው ጋር ነው። ከነዓናዊቱ ሴት፡- “የልጆችን እንጀራ ይዞ ለውሾች (የሴምን በረከት ለከነዓን) መስጠት አይገባም፤” በተባለች ጊዜ፡- “አዎን ጌታ ሆይ፥ ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ፤ (የጻድቅ በረከት ለኃጥእ ይተርፋል፤ እንዲል፡- የሴም ልጆች በረከት፥ እርግማን ለወደቀባቸው ለከነዓን ልጆችም ተርፎ ጾም አያድሩም)፤” ያለችው ለዚህ ነው። ማቴ: ፲፭፥፳፮። ምክንያቱም፡- ውሻ ከጌታው ጋር በቤት እንደሚኖር፥ ጻድቁ ኖኅ የረገመው ከነዓንም እንደ ልጅ ሳይሆን፥ ለወንድሞቹ የባሪያ ባሪያ ሆኖ በቤት እንዲኖር ተፈቅዶለታልና ነው። ዘፍ፡፱፥፳፰። ይልቁንም አሁን ባለንበት ዘመናዊ ዓለም፡- ወንጀልን ለመቆጣጠር እና ለመከታተል፥ ከቴክኖሎጂው ይልቅ ውሻ አስተማማኝ ረዳት ሆኖ ተገኝቶአል። በክፉ ምሳሌነቱ ደግሞ፡- እንደ ርኵስ ስለ ተቆጠረ በቅድስናው ስፍራ እንዲቆም አልተፈቀደለትም። በዚህም ለመናፍቃን እና ለአሕዛብ ምሳሌ ሆኖአል። “በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ የተቀደሰ ውን ለውሾች አትስጡ፤” ይላል። ማቴ፡፯፥፮። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም፡- “ከውሾች ተጠበቁ፤” ብሎአል። ፊል፡፫፥፪። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ፡- ፈጥነው የሚክዱትን ሰዎች በውሾች መስሎ፡- “በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርስዋ ተጠላልፈው የተሸነፉ ቢሆኑ ከፊተኛው ኑሮአቸው ይልቅ የኋለኛው የባሰ ሆኖባቸዋል። አውቀዋት ከተሰጣቸው ከቅድስት ትእዛዝ ከሚመለሱ የጽድቅን መንገድ ባላወቋት በተሻላቸው ነበርና። ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፥ ደግሞ፡- የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለ ሳለች እንደሚል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋለ።”በማለት ተናግሮአል።፪ኛ፡ጴጥ፡፪፥፳።ባለ ራእዩ ቅዱስ ዮሐንስም፡- ወደ መንግሥተ ሰማያት [...]
Tue, Jan 26, 2016
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፡-ገና በሦስት ዓመቷ ለእግዚአብሔር ተስጥታ፥ ያደገችው በቤተ መቅደስ ውስጥ ነው። ቅዱሳን መላእክት እየመገቧት፥እየዘመሩለት እና እየሰገዱላት ዓሥራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ ኖራለች።ቅዱስ አባ ሕርያቆስ፡- በቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ፥ መንፈስ ቅዱስ ቢገልጥለት፥ አስተዳደጓ እንዴት እንደነበረ ከሌሎቹ እያነጻጸረ ተናግሮአል። “ድንግል ሆይ! አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ (አታሞ እየመቱ፥ እስክስታ እየወረዱ እንደሚያድጉ) እንደ ዕብራውያን ልጆች በቧልት (በቀልድ፥በፌዝ) በጨዋታ ያደግሽ አይደለም፤ በቅድስና፥ በንጽሕና በቤተ መቅደስ ውስጥ ኖርሽ እንጂ። ድንግል ሆይ! ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለሽም፥ ከሰማይ የተገኘ (በጥበብ አምላካዊ የተሠራ) ኅብስትን ተመገብሽ እንጂ።ድንግል ሆይ! ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለሽም፥ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ (ከሰማይ የተገኘ) ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ፤” በማለት አድንቆአል። ይኸውም ወደ ቤተ መቅደስ በገባችበት ዕለት፥ ቅዱስ ፋኑኤል ሲመግባት በገሀድ ከታየበት ጊዜ ጀምሮ እሰከ መጨረሻው የዘለቀ ነው። [...]
Sat, Jan 16, 2016
“በመከራዬ ጊዜ በአፌ የተናገርሁትን፥ ከንፈሮቼም ያሉትን ስእለቴን ለአንተ እፈጽማለሁ፤ ”መዝ፡፷፭፥፲፬። በአምላክ ኅሊና ተቀርፃ የኖረች ጽላት፥ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፡- የብጽዓት ልጅ ናት። ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና፡- “ወንድ ልጅ ብንወልድ፡- ወጥቶ ወርዶ፥ አርሶ ቆፍሮ ይርዳን አንልም፤ ለቤተ እግዚአብሔር እንሰጠዋለን። ሴት ልጅም ብንወልድ፡- እንጨት ሰብራ ውኃ ቀድታ፥ ፈጭታ ጋግራ ታገልግለን አንልም፤ ለቤተ እግዚአብሔር እንሰጣታለን።” ብለው ተስለው ነበር። በመሆኑም፡- ገና በሦስት ዓመቷ ለቤተ እግዚአብሔር ሊሰጧት ተስማሙ። ይህም፡- ሕልቃና እና ሐና፥ ነቢዩ ሳሙኤልን፡- ለቤተ እግዚአብሔር ለመስጠት እንደተስማሙት አይነት ነው። ሐና ሕልቃናን፡- “ሕፃኑ ጡት እስኪተው ድረስ እቀመጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ በእግዚአብሔር ፊት ይታይ ዘንድ፥ በዚያም ለዘለዓለም ይሆን ዘንድ አመጣዋለሁ።” እንደ አለችው፥ ቅድስት ሐናም ቅዱስ ኢያቄምን፡- “ይህች ብላቴና ሆዷ ዘመድ ሳይወድ፥ አፏ እህል ሳይለምድ ወስደን አንሰጥምን? "የሰጠ ቢነሳ የለበትም አበሳ፤» እንደሚባለው፥ አንድ ነገር ብትሆንብን ከልጃችንም ከእግዚአብሔርም ሳንሆን እንቀራለን፤” ብለዋለች። በኦሪቱ ዘመን ሕልቃና ለሐና፡- “በዓይንሽ ደስ ያሰኘሽን አድርጊ፥ ጡትም እስኪተው ድረስ ተቀመጪ፤ ብቻ እግዚአብሔር ቃሉን ያጽና፤” [...]
Sat, Jan 09, 2016
ብርሃነ ልደቱ ለእግዚእነ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ“ሕዝብ ዘይነብር ውስተ ጽልመት ርእየ ብርሃን ዓቢየ ወለአለሂ ይነብሩ ውስተ ጽልመት ወጽላሎተ ሞት ብርሃን ሠረቀ ሎሙ” በድንቁርናና በቀቢጸ ተስፋ ለነበሩ ሰዎች ፍጹም እውቀት ተሰጣቸው፤ ሞት ባመጣው ምስል ሞትን በመምሰል ለነበሩ ሰዎች ክርስቶስ ተወለደላቸው በሞተ ሥጋ በሞተ ነፍስ ለነበሩ ልጅነት ተሰጣቸው፤ በኃጢአት ለነበሩ ስርየት፤ በክህደት ለነበሩ ሃይማኖት ተሰጣቸው ኢሳ.ም 9፣2እግዚአብሔር የሁላችን አባት አዳምን በአርአያውና በመልኩ ከፈጠረው በኋላ ባረከው ሁሉንም እንዲገዛ እንዲነዳ ሥልጣን ሰጠው፤ በረከቱን፣ ሥልጣኑንና ሲሳዩን ከሰጠው በኋላ ፈጣሪውን የሚያስታውስበት ትዕዛዝ አዘዘው፡፡ ትዕዛዙም የፈጣሪና የፍጡር መለያ፣ የአዛዥና የታዛዥ ገደብ፣ ሰው ለሕግ መገዛት እንደሚገባው ለማስረዳት የተደረገ እንጂ የስስት ወይም የንፍገት አልነበረም፡፡ ይህንን ደግሞ አዳምም ሆነ ሔዋን ያውቁታል፤ በምግብ እጦት እንዳይቸገሩ ግን በገነት ያሉትን አትክልት እንዲበሉ ከውኃውም እንዲጠጡ ፈቅዶላቸዋል፡፡ሰው ግን ከፍጥረት አክብሮ አልቆ ያነገሠውን እግዚአብሔርን አስቀይሞ በተሳሳተ ምክር ተመርቶ አትብላ የተባለውን ዕፀበለስን ስለበላ ከፈጣሪውም ትዕዛዝ ስለወጣ በዚህ ምክንያት የሞት ፍርድ ተፈረደበት፡፡ ከኤዶም ገነት ተባረረ፣ ከአምላኩ ጋር ተጣላ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው አንድነት ግንኙነት ተቋረጠ “ወደ ወጣህበት ምድር እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ” ዘፍ 3፣19አለው ጥሮ ግሮ እንዲበላ የፈቀደለት የገነት ፍሬ ሳይሆን የተፈጠረባት ምድር ላይ እኛ የምንመገበውን ዕፅዋቱን፣ አዝዕርቱን፣ አትክልቱን፣ እንሰሳቱን ምግበ ሥጋ የሆነውን ሁሉ ነው፡፡እንደ መላእክት ማመስገን፣ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገርን፣ ልጄ ወዳጄ መባልን፣ በቅድስና [...]
Fri, Sep 11, 2015
ጥምቀተ ክርስቶስ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም በጤና አደረሰንበኢትዮዽያ አኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት እና ስርዓት መሰረት በየዓመቱ ጥር 11 ቀን በታላቅ ድምቀት የጥምቀት በዓል ይከበራል ለመሆኑ ጥምቀት ምን ማለት ነው ? እና በሌሎች በጥምቀት ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እንሞክራለን ጥምቀት የሚለው ቃል አጥመቀ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም መላ ሰውነትን በተቀደሰ ውኃ መነከር ወይም መዘፈቅ ውሰጥ ገብቶ መውጣት መነከር መውጣት መቀበር ማለት ነው አንድ ሰው በመጠመቁ ክርስቶስን በሞቱ ይመስለዋል ይኸውም ተጠማቂው ከቅዱሱ ውኃ ሲነከር በክርስቶስ ሞቶ ሲመስለው ከውኃ ሲወጣ ደግሞ ክርስቶስን በትንሣኤው [...]
Fri, Sep 11, 2015
የቤተክርስቲያን የቀን መቁጠሪያን ያዘጋጀ ድሜጥሮስ ሊቀ ጳጳስ ነው!ድሜጥሮስ ማለት መስተዋት ማለት ነው፡፡ ሀገሩ እስክንድርያ ነው፡፡ አባት እናቱ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋጎች ነበሩ፡፡ ላባቱ ወንድም ሴት ልጅ ነበረችው ሲሞት ልጄን ከልጅህ አትለይብኝ ብሎት አብሮ አሳድጓቸዋል፡፡አካለ መጠን ሲያደርሱ ዘመኑ አረማውያን የበዙበት አማንያን ያነሱበት ነበርና ከሌላ ብናጋባቸው ከሃይማኖት ከገቢረ ሠናይ ይርቃሉ፤ ሕገ ነፍስ ከሚፈርስ ሕገ ሥጋ ይፍረስ ብለው አጋቧቸው፡፡ በልተው ከጠገቡ ጠጥተው ከረኩ በኋላ ሥርዓተ መርዓዊ ወመርዓት ያድርሱ ብለው መጋረጃ ጣሉባቸው፡፡ እሷ አስቀድማ ድሜጥሮስ ያንተ ወንድምነት ለኔ የእኔ እኅትነት ላንተ አልበቃ ብሎ የባዕድ ሥራ እንሥራ አለችው፡፡ እኔስ የአባት የእናቴን ፈቃድ ልፈጽም ብዬ እንጂ ፈቃዴ አይደለም፤ በዚያውስ ላይ አንቺ ከፈቀድሽ ብንተወው እንችል የለምን? አላት እንተወው አለችው፡፡ እንኪያስ አንቺንም ለሌላ እኔንም ለሌላ እንዳያጋቡን መስለን እንኑር አላት፡፡ በዚህ ተስማምተው አንድ ምንጣፍ እያነጠፉ አንድ ዐጽፍ እየተገናጸፉ 48 ዘመን ኖሩ ፡፡ ምነው “መኑ ይክል ሐቁረ. እሳት በሕጽኑ ይል የለምን እንደምን ይቻላል? ቢሉ ሕሩይ ለንጽሕና ነውና አንድም እሳቱን እንዲታፈኑ ማድረግ ለጌታ ይሳነዋልን? መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ቀኝ ክንፉን ለርሱ ግራ ክንፉን ለርሷ አልብሶ አድሮ ሲነጋ በአምሳለ ርግብ በመስኮት ወጥቶ ሲሄድ ያዩት ነበር፡፡ በዘመኑ የነበረ ሊቀጳጳስ ሉክዮስ /ሉክያኖስ/ ይባላል፣ አረጀ ደከመ፡፡ ሕዝቡን ሰብስቦ እኔ አርጅቻለሁና ከኔ ቀጥሎ የሚሾምላችሁን ምረጡ አላቸው፡፡ [...]
Fri, Sep 11, 2015
በኩረ ትንሳኤ ክርስቶስ “ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን“ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሠሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ [...]
Fri, Apr 25, 2014
የተወደዳችሁ ምእመናን እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ አሸጋገራችሁ! ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን ለሚገኙ ምእመናን መጪው ጊዜ ምን እንደሚመስል ከገለጠላቸው በኋላ አያይዞ እንዴት መኖር እንዳለባቸው መክሮአቸዋል፡፡ ስለመጪው ጊዜ ሲነግራቸው ‹‹ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና›› ብሏቸዋል፡፡ዘመነ ሰላም ያድርግልን 2005እንዴት መኖር እንዳለባቸው ሲመክራቸው ደግሞ ‹‹እንደጥበበኞች›› በጥበብ መመላለስ እንደሚገባቸው፤ ዳግመኛም ‹‹በጥንቃቄ›› እና ‹‹በመጠበቅ›› እየኖሩ ዘመኑን እንዲዋጁ አሳስቧቸዋል፡፡ (ኤፌ5.15-16) እነዚህ ቁም ነገሮች ለጊዜው በኤፌሶን ላሉ ምእመናን ቢጻፉም ለሁላችን ምክር እና እዝናት የሚሆኑ ናቸውና በየተራ እንመለከታቸዋለን! ‹‹ቀኖቹ ክፉዎች ናቸው›› ማለት ምን ማለት ነው? የቀን ክፉ አለን? ብለን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ በእርግጥ ክፋት አስቦና ፈቅዶ በሚበድል በሰው ልጅ ዘንድ እንጂ በቀናት ዘንድ ክፋት የለም፡፡ ዕለታትን የፈጠረ እግዚአብሔር ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ደግሞ ‹‹እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም ነው›› (1ጢሞ4.4) ስለዚህ ዕለታት በሙሉ በተፈጥሮ አንድ ናቸው፤ እንዲሁም ሁሉም መልካም ናቸው፡፡ የዕለታት መልካቸው የሰው ልጅ ምግባር ነው፡፡ የሰው ሥራ ክፉ የሆነ እንደሆነ ዕለታትም ይከፋሉ፡፡ ሰው መልካም ሲሆን ዘመናቱ መልካም ይሆኑለታል፡፡ ሐዋርያው በዕለት አንጻር የሰውን ክፉነት ሲነግረን ‹‹ቀኖቹ ክፉዎች›› ናቸው አለን፡፡ በጸሎተ ቤተ ክርስቲያን ‹‹እግዚኦ አድኅነነ እምዕለት እኪት ወባልሃነ እምኩሉ መንሱት›› - ‹‹አቤቱ ከክፉ ቀን ከፈተናም ሁሉ ፈጽመህ አድነን፡፡›› የሚል ኃይለ ቃል እናገኛለን፡፡ አበው ካህናት ሲያሳርጉ ‹‹ከዕለት እኪት ከዘመን መንሡት ይሰውረን!›› የሚሉት እነዚህን [...]
Fri, Apr 25, 2014