Quiz1

መልስ የሚሆኑትን ሁሉ ምረጥ

1. ሃይማኖት ማለት
ሀ/ ማመን ለ/ መታመን ሐ/ ተአማኒነት መ/ አመኔታ

2. የሰው ልጅ እግዚአብሔርን በምን ይመስለዋል
ሀ/ በዕውቀት ለ/ በአገዛዝ መ/ በመልክ መ/ በነፍስ

3. ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ያልተጠመቀ ይፈረድበታል የሚለው ቃል የት ይገኛል
ሀ/ ማቲዎስ ለ/ ማርቆስ ሐ/ ሊቃስ መ/ ዮሐንስ

4. ከሚከተሉት የትኛው ስሕተት ነው
ሀ/ ሃይማኖት እባቡን ለመርገጥ ጊንጡን ለመጨበጥ መርዝን ለመጨለጥ ዲያቢሎስን ድል ለመንሳት አጋነንትን ለመግዛት ስልጣን ትሰጣለች
ለ/ ሃይማኖት የሚገለጠው በምግባር ነው
ሐ/ ምግባር ያለ ሃይማኖት ሊሰራ አይችልም
መ/ ሃይማኖት የፍጡር ሕሊና መርምሮ የማይፈጽማት ምስጢር ናት

5. የሃይማኖት ጥቅም የሆነው
ሀ/ ሰው ተፈጥሮውን ምንነቱን አቅሙን ይሚያውቅበት የሚረዳበት ነው
ለ/ ሰው ከሞተ ነፍስ ከደዌ ሥጋ የሚድንበት ነው
ሐ/ ሃይማኖት በትንሣኤ ሙታን ማመን ነው
መ/ሰው እየሱስ ክርስቶስ በምድር የሰራውን ከዛም የሚበልጥ መስራት ታስችላለች
ሠ/ ሃይማኖት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚይያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው