ትምህርት

Earlier
                   የቤተክርስቲያን የቀን መቁጠሪያን ያዘጋጀ  ድሜጥሮስ ሊቀ ጳጳስ  ነው!ድሜጥሮስ ማለት መስተዋት ማለት ነው፡፡ ሀገሩ እስክንድርያ ነው፡፡ አባት እናቱ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋጎች ነበሩ፡፡ ላባቱ ወንድም ሴት ልጅ ነበረችው ሲሞት ልጄን ከልጅህ አትለይብኝ ብሎት አብሮ አሳድጓቸዋል፡፡አካለ መጠን ሲያደርሱ ዘመኑ አረማውያን የበዙበት አማንያን ያነሱበት ነበርና ከሌላ ብናጋባቸው ከሃይማኖት ከገቢረ ሠናይ ይርቃሉ፤ ሕገ ነፍስ ከሚፈርስ ሕገ ሥጋ ይፍረስ ብለው አጋቧቸው፡፡ በልተው ከጠገቡ ጠጥተው ከረኩ በኋላ ሥርዓተ መርዓዊ ወመርዓት ያድርሱ ብለው መጋረጃ ጣሉባቸው፡፡ እሷ አስቀድማ ድሜጥሮስ ያንተ ወንድምነት ለኔ የእኔ እኅትነት ላንተ አልበቃ ብሎ የባዕድ ሥራ እንሥራ አለችው፡፡ እኔስ የአባት የእናቴን ፈቃድ ልፈጽም ብዬ እንጂ ፈቃዴ አይደለም፤ በዚያውስ ላይ አንቺ ከፈቀድሽ ብንተወው እንችል የለምን? አላት እንተወው አለችው፡፡ እንኪያስ አንቺንም ለሌላ እኔንም ለሌላ እንዳያጋቡን መስለን እንኑር አላት፡፡ በዚህ ተስማምተው አንድ ምንጣፍ እያነጠፉ አንድ ዐጽፍ እየተገናጸፉ 48 ዘመን ኖሩ ፡፡ ምነው “መኑ ይክል ሐቁረ. እሳት በሕጽኑ ይል የለምን እንደምን ይቻላል? ቢሉ ሕሩይ ለንጽሕና ነውና አንድም እሳቱን እንዲታፈኑ ማድረግ ለጌታ ይሳነዋልን? መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ቀኝ ክንፉን ለርሱ ግራ ክንፉን ለርሷ አልብሶ አድሮ ሲነጋ በአምሳለ ርግብ በመስኮት ወጥቶ ሲሄድ ያዩት ነበር፡፡                   በዘመኑ የነበረ ሊቀጳጳስ ሉክዮስ /ሉክያኖስ/ ይባላል፣ አረጀ ደከመ፡፡ ሕዝቡን ሰብስቦ እኔ አርጅቻለሁና ከኔ ቀጥሎ የሚሾምላችሁን ምረጡ አላቸው፡፡     አባታችን አንተው ግብር ገብተህ ቀኖና ይዘህ ንገረን እንጂ እኛ ምን እናውቃለን አሉት፡፡ ቀን [...]
Thu, Sep 10, 2015
            ጥምቀተ ክርስቶስ                                       እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም በጤና አደረሰን በኢትዮዽያ  አኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት እና ስርዓት  መሰረት በየዓመቱ ጥር 11  ቀን በታላቅ ድምቀት የጥምቀት በዓል ይከበራል ለመሆኑ ጥምቀት ምን ማለት ነው ? እና በሌሎች በጥምቀት ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እንሞክራለን                                                                              ጥምቀት የሚለው ቃል አጥመቀ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም መላ ሰውነትን በተቀደሰ ውኃ መነከር ወይም መዘፈቅ ውሰጥ ገብቶ መውጣት መነከር መውጣት መቀበር ማለት ነው አንድ ሰው በመጠመቁ ክርስቶስን በሞቱ ይመስለዋል ይኸውም ተጠማቂው ከቅዱሱ ውኃ ሲነከር በክርስቶስ ሞቶ ሲመስለው ከውኃ ሲወጣ ደግሞ ክርስቶስን በትንሣኤው ይመስለዋል፤ በዚህም ከክርስቶስ ጋር አንድ ይሆናል፡   “እንግዲህ ክርስቶስ ከሙታን እንደተነሣ፤ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን፡ ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን” እንዲል፡፡ /ሮሜ.፮፥፬ ቆላ. ፪ ፥፲   ጌታለምንተጠመቀ?     ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እጸድቅ አይል ጻድቅ፤ እከብር አይል ክቡር፣ እቀደስ አይል ቅዱስ የነገሥታት ንጉሥ፣ የኃያላን ኃያል፣ የአማልክት አምላክ፣ የቅዱሳን ቅዱስ (ቅድስናው የባሕሪው የሆነ) የአሸናፊዎች አሸናፊ፣ የባሕርይ አምላክ የሁሉ ጌታ ሲሆን፤ ለምን ተጠመቀ ቢሉ ሮሜ፱፥፭፣ ፩ዮሐ ፭፥፳፣ ፩ተሰ ፫፥፲፩፣ ቲቶ፪፥፲፩፣ ኢሳ ፱፥፮፣ ፩ጢሞ ፮፥፲፭፣ ራእይ ፲፱፥፲፩-፲፮/ ፩ኛ. ለአብነት /ምሳሌ/ ለመሆን፡- ጌታችን በዚህ ምድር በሥጋው ወራት የፈጸማቸው ትሩፋቶች ለኛ ምሳሌ ይኾነን ዘንድ ነው፡ የደቀ መዛሙርቱን እግር በትሕትና ካጠበ በኃላ፥ “እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርሰ በእርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኃል፡ እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሣሌ ሰጥቻችኋለሁና” ብሎ እንደ ተናገረ፡;ዮሐ. ፲፫፥፫ ፬/ ይህንንም ቅዱሳን ሐዋርያት በትምህርታቸው መስክረዋል፡፡ ፩ዮሐ፪፥፮፣፩ጴጥ፪፥፳፩፣ዕብ፲፪፥፩፫/ ጌታችን ጾምን፣ ጸሎትን በተግባር ከነሥርዓቱ አስተማረን፤ በቃሉም አዘዘን “ባልዋጁባት ጣት የዘንዶ ጉድጓድ ይሰድዱባት” እንዲሉ፥ ጌታችን እርሱ ሳይፈጸም ትእዛዛቱን፣ ሕግጋቱን ፈጽሙ አላለንም፡፡ በተግባር ያሳየንን አዘዘን እንጂ፡፡“የሃይማኖታችን ራስና ፈጻሚ” ተባለ ፡፡ ዕብ.፲፪፥፩፪ የሃይማኖታችንራስየሃይማኖታችን መሠረት/ ማለት ሲሆን፤ ፈጻሚ ማለቱ፥ የክርስትና ሃይማኖት መሠረታዊ ሕግጋትን አድራጊ ማለት ነው፡፡ ፪ኛ፡- ጥምቀታችንን ሊባርክ /ሊቀድስ/፣ ለጥምቀታችን ኃይልን ሊሰጥ /ለመስጠት/ ከጥንት ጀምሮ እስከ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ጊዜ የነበረው የጥምቀት ሥርዓት ለአማናዊው የክርስቶስ ጥምቀት ምሣሌ ነበር፡ ከሥጋ ደዌና መቅሰፍት የሚዳንበት እንጂ፣ ልጅነትን የሚያሰጥ፣ መርገመ ሥጋንና ነፍስን ማራቅ የሚቻለው አልነበረም፡ ጌታችን ከተጠመቀልን በኃላ ግን፤ ተጠምቀን በሥጋ በነፍስ የምንከብርበት፣ ጸጋ ሥርየት ኃጢኣትን/ የምንጐናጸፍበትና፣ የመንግሥተ ሰማያት ዕጩዎች የምንሆንበትን ስጦታ የተቀበልንበት ነውና በዓላችን ብለን እናከብረዋለን፡፡ /ዮሐ ፩፥፳፮፣ የሐ/ሥራ ፲፥፴፬—፴፱፣፲፱፥፩—፫/ ፫ኛ ምሥጢራትን ለመግለጽ፤ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተጠመቀ ጊዜ ለዘመናት ተሠውሮ የነበረው የአንድነትና የሦስትነት ምሥጢር (ምሥጢረ ሥላሴ) ገሃድ ኾኖ ተሰበከ፡ ይኸም ብቻ ሳይሆን የክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት (የአብ ልጅ የድንግል ልጅየድንግል ልጅ የአብ ልጅ መሆኑ) በአብ በመንፈስ ቅዱስ የተመሰከረበት ዕለት ነውወልድ ክርስቶስ ተብሎ በአካለ ሥጋ አብ በደመና ኾኖ፣ መንፈስ ቅዱስ በርግብ ምሣሌነት ሦስት አካላት በአንድ አምላክነት ተገለጹ፡ ክርስቶስ የተባለው የድንግል ልጅ እግዚአብሔር አብ ከባሕርይ የወለደው ስለመሆኑም፥ አንዱን ባሕርይ በተዋሕዶ “ልጄ” ብሎ በመጥራቱ፥ ሃይማኖት ታወቀ፤ ተረዳ፡ የቀናውን ኦርቶዶክስ/ እምነት “ተዋሕዶ” ተብሎ የተጠራውም በዚህ መሠረትነት ነውማቴ ፫፥፲፫፲፯ ማር ፩፥፱ ፲፩ ሉቋ ፫፥፳፬፣ ዮሐ ፫፥፲፮-፲፰፣ ዕብ ፪፥፩-፫፣ኤር ፮:-፲፮ የሐ/ሥራ ፲፫:-፲)                     ጌታችን ለምን በ፴ ዘመኑ ተጠመቀ? ፩ኛ፡- ለካሣ ነው፡፡ካሣ ማለት ለተበደለ አካል የሚቀርብ የነፍስ ዋጋ ፈላማ/ ማለት ነው፡፡ ጌታችን በ፴ ዘመኑ የተጠመቀው፤ አዳም ከእግዚአብሔር በተፈጠረ በ፴ ዘመኑ ያገኘውን ልጅነት በዲያብሎስ በተሠወረበት በከይሲ በእባብ/ ምክር ተታሎ አስወስዶ ነበርና፤ እርሱም በ፴ ዘመኑ ተጠምቆ የዲያብሎስን ሥራ አጥፍቶ÷ ልጅነቱን ሊመልስለት በ፴ ዘመኑ ተጠመቀ፡ በዚህም ዳግማዊ አዳም /ሁለተኛ አዳም/ ተባለ፡፡ /፩ኛ ቆሮ. ፲፭፥፵፭—፵፮/ ፪ኛ. ሕግን ለመሥራት ነው በብሉይ ኪዳን ለመንፈሳዊ አገልግሎትና ሕግ ለማድረስ የሚታጩበት   የሚመረጡበት/ ከ፴ ዓመታቸው ጀምሮ ነበር።ዘኁ. ፬፥፫፵፯/ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የሕግ ባለቤት እንደመሆኑ፥ ማስተማር የጀመረው በ፴ ዕድሜው ነው፡ ሉቋ. ፫፥፳፩/ በዚህም መነሻነት በሐዲስ ኪዳን ሰዎች ለመንፈሣዊ ተግባር መመረጥ ያለባቸው በዕድሜያቸው ልክ ሙሉ ሲሆኑ፤ ኃላፊነት ለመሸከም በሚችሉበት የዕድሜ ልክ የዕውቀት፣ የብስለት ደረጃ ሲደርሱ መሆን እንዲገባው÷ ጌታችን በተግባር አሳየን፡፡                   ጌታችን ወደ ዮሐንስ ሄዶ ለምን ተጠመቀ ? ጌታችን የዮሐንስ ጌታ፣ ፈጣሪ ነው፡፡ ዮሐንስ አስቀድሞም ሰለእርሱ ሲመሰክር፡- “አንድ ሰው ከእኔ በኋላ ይመጣል÷ ከእኔም በፊት ነበረና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኗል ብዬ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነው” ዮሐ ፩÷፳፱/“ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣሙ ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል” ማቴ. ፫፥፲፩/  በማለት የክርስቶስን ቀዳማዊነት፣ ልዕልና መስክሯል፡፡ ወደ እርሱ ሊጠመቅ በመጣ ጊዜም “እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር” ተብሎ ተጽፏል፡፡ /ማቴ ፫፥፲፬/    ጌታችን የባሕርይ ጌታ /ፈጣሪ/ ሆኖ ሳለ፥ ስለምን ወደ ዮሐንስ ሄዶ ተጠመቀ ቢሉ፡- ፩ኛስለትሕትናነው ጌታችን “ከእኔም ተማሩ ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና” ማቴ. ፲፩፳፱/ ብሎ በቃል ያስተማረውን በተግባር ሲያሳየን፤ አገልጋዩ የኾነውን ቅዱስ ዮሐንስ ወደ እኔ ይምጣ ሳይል፣ እርሱ ግን ቅዱስ ዮሐንስ ካለበት ድረስ ሄደ፡ ከእርሱ በላይ ካህን፣ መምህርጌታ፣ ንጉሥ ከወዴት አለ? ምንም እንኳን ሰዎች ቢያከብሩንም ራሳችንን በትሕትና ማዋረድ እንዲገባን ጌታችን አስተማረን፡ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ አንተ በእኔ ልትጠመቅ አይገባህም እኔ በአንተ እንጂ ባለው ጊዜ ጌታችን አሁንስ ፍቀድልኝ እንጂ ጽድቅን/የነቢያት ትንቢትን/ መፈጸም ይገባናል አለው ተብሎ ተጽፏልና፡፡ (ማቴ. ፫፥፲፬) ፪ኛ፡ ሥርዓትን ለመሥራት  ጌታችን እንደ ጌትነቱ ቅዱስ ዮሐንስ እርሱ ዘንድ መጥቶ እንዲያጠምቀው ቢያዘው ኖሮ፤ በየዘመኑ የሚነሡ ነገሥታት፣ ባለጠጎች ምእመናን አጥማቂ ካህናትን በቤተ መንግሥታችን፣ በእልፍኛችን መጥታችሁ አጥምቁን፤ ልጆቻችንንም አጥምቁልን ባሏቸው ነበር፡ ጌታችን ግን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ወዳለበት ባሕረ ዮርዳኖስ ሄዶ በመጠመቁ ምእመናን ካህናት ወደ ተሰየሙበት ቅድስት ቤተክርስቲያን ዘንድ ሄደው እንዲጠመቁ ምክንያት ሆኖ ሥርዓትን ሠራልን                 በጥምቀት ምን ጸጋ ይገኛል ? ጥምቀት  የተፈጸመለት ተጠማቂ ልዩልዩ  ጸጋዎችን ያገኛል  ሀ.ክርስቶስን እንለብሳለን  ሐዋርያው “ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን  ለብሳችሁታልና” /ገላ.፫፥፳፯/ ብሎ እንደተናገረ፡፡ ለ. በጥምቀት ከእግዚአብሔር በጸጋ እንወለዳለን፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ “በስሙ ለሚያምኑት ለእርሱ የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይንም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም” ብሎ እንዳስተማረ፡፡ /ዮሐ.፩፥፲፩—፲፭/ ሐ.በጥምቀት ድኅነትይገኛል ያለ  ጥምቀት   መዳን የለም “ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ /አምኖ  ያልተጠመቀ/ ይፈረድበታል” ተብሎ እነደተጸፈ፡፡ /ማር.፲፮፥፲፮/ መ.ስርየኃጥያትንያሰጣል  በመጀመሪያይቱ የቤተክርስቲያን የልደት ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት  ሦስት ሺህ ሰዎች አምነው “እንድን ዘንድ ምን እናድርግ ?” ቢሉት ፤ “ንሥሐ ግቡ፥ ኃጢኣታችሁም ይሠረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታን ትቀበላላችሁ” አላቸው፡ /የሐ/ሥራ ፪፴፷/ ከቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት በጥምቀት ኃጢኣት እንደሚሠረይ፣ የመንፈስ ቅዱስንም ጸጋ መቀበል እንደሚቻል፣ መረዳት ይቻላል፡፡  ሠ.የክርስቶ ደቀመዝሙር ያደርጋል   ጌታችን ቅዱሳን ሐዋርያትን ወንጌልን እንዲያስተምሩ ወደ ዓለም ሲልካቸው “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥… ደቀ መዛሙርቴ አድርጓቸው”ሜቴ ፳፷፲፱/ ብሎ አዝዟቸዋል፡ እነርሱም በዚህ ትእዛዝ መሠረት ዓለምን ዙረው አስተምረው፤ አሳምነው፤ አጥምቀው፤ ሰዎችን ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፤ ከሞት ወደ ሕይወት፤ ከክህደት ወደ ሃይማኖት፤ ከጥርጥር ወደ እምነት፤ መልሰዋል፡ ጥምቀት ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን ለመመለሳችን ማረጋገጫ ማኀተም ነውና፡፡ /የሐ/ሥራ ፰፥፴፰ ፣፲፮፥፲፮፥፲፭—፴፫/                                    ከተራ ምን ማለት ነው ? ከተራ፡ ቃሉ እንደሚያመለክተው የሚፈስ ውኃ በአንዳች ነገር መዝጋት፣ ማቆም፣ መከልከል ማለት ሲሆን፤ በዓሉየጥምቀትውሃና ባሕሩን/ የሚከተርበት ዕለት መሆኑን ያለመከታል፡ ይህውም ጥር ፲ ቀን የጥምቀት ዋዜማ ነውበዘመነ ኦሪት  የእግዚአብሔር ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግር ጫማ በዮርዳኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም ውኃው ቦታእንደሚከትርእንደሚከማች/ ተነግሯቸው ነበር ይህም ተፈጽሟል፡፡ ኢያሱ ፫፥፲፫፲፮/ በሀገራችን ይህ በዓል ሲከበር ኖሯል፡ ኋላም በዘመነ ክርስትና ቤተክርስቲያን በምሥጢር አስማምታ በሐዲስ ሥርዓት ታክብራለችበዚህም ዕለት ታቦታት ሕጉ ከመንበረ ክብራቸው ተነሥተው ወደ ተዘጋጀው ባሕረ ጥምቀት ይሻገራሉ፡ ይህም ጌታችን ከገሊላ ተነሥቶ ወደ ዮርዳኖስ መጓዙን የሚያስታውስ ሥርዓት ነው፡፡ /ማቴ. ፫፥፲፫ ፣ ማር.፩፥፱/                            የጥምቀት ጾም/ጾመ ገሃድ የጥምቀት ጾም የምንለው በከተራ በሚውልበት ቀን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ሆኖ ጾመ ገሃድ በመባል የምንጾመው ሲሆን ይህም ከጌታችን ዐበይት በዓላት አንዱ ጥምቀት በመሆኑ በዚህ ታላቅ በዓል በፍጹም ደስታ እንድናከብረው ስርዓተ ቤተክርስቲያን ስለሚያዝ የከተራ ዕለት  የገሃድ ጾም ይጾማል፡፡ የከተራ ዕለት ሰንበት ካልሆነ በቀር፤ ሁል ጊዜም ጾም ሆኖ ይውላል፡፡ በዓለ ጥምቀት ፡-  ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ፴ ዘመኑ በእደ ዮሐንስ፣ በማየ ዮርዳኖስ በዘመነ ሉቃስ ማክሰኞ ጥር ፲፩ ቀን እኩለ ሌሊት የተጠመቀበት ዕለት ነው፡ በዋዜማው በወንዝ ዳርበሰውሠራሽየውኃግድብበዳስ በድንኳን/ ታቦቱ ካደረ በኋላ፤ ሌሊቱን ስብሐተ እግዚአብሔር ሲደረስ አድሮ፤  ሥርዓተ ቅዳሴውም ይፈጸማል፡ ይህም የክርስቶስን የጥምቀት ጊዜን የሚያዘክር ነውበወንዙ ዳር በግድቡ/ ጸሎተ አኰቴት ተደርሶ፣ አራቱም ወንጌላት ከተነበበ በኋላ ውኃው ተባርኮ ለተሰበሰበው ሕዝብ ይረጫል፡ ይህም የተጠመቀውን ሕዝብ ድጋሚ ለማጥመቅ የተደረገ ሳይሆን ጌታችን ለኛ ብሎ ያሳየውን ትሕትና ለመመስከርና ከበረከተ ጥምቀቱ ምእመናን ለማሳተፍ የተደረገ ሥርዓት ነው፡፡                           ቃና ዘገሊላ ምን ማለት ነው ? ቃናዘገሊላ፡- በጥምቀት ማግስት በተጠራበት ቤት ውኃን የወይን ጠጅ ያደረገበት ተአምር የሚዘከርበት በዓል ነው፡፡ በወንጌል እንደተጻፈው “በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሠርግ ነበር” እንዳለ፡ ጌታችን በጥር ፲፩ ሌሊት እንደተጠመቀ ልዋል ልደር ሳይል ዕለቱን ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ ሄዶ ፵ መዓልትና ሌሊት ጾሞ ከገዳምሲወጣ ቀኑ የካቲት ፳ ይሆናል፡ በሦስተኛ ቀን የተባለውም ከገዳም ከወጣ በኋላ ያለው ተቆጥሮ ነው ቀኑም የካቲት ፳፫ ቀን ይሆናል፡ የቃና ዘገሊላ በዓል ዐቢይ ጾም ላይ ስለሚውልና ለማክበር ስለማይመች የውኃን በዓል ከውኃ ጋር ቢያከብሩት ይስማማልና በማለት ከጥምቀቱ ጋር አስጠግታ ቅድስት ቤተክርስቲያን  ጥር12ቀንታከብራለ(ዮሐ. ፪፩፲፩)እኛም በዚህች በጸናች በጎላች በተረዳች በንጽሕትተዋሕዶ ሃይማኖታችንና ምግባራችን ጸንተን የክብሩ ወራሾች እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር ቸርነት ፤ የድንግል እናቱ ጸሎት ፤ የጻድቁ አባታችን ተክለሃይማኖት አማላጅነት አይለየን! አሜን፡፡                      [...]
Sat, Jan 17, 2015
                                        ብርሃነ ልደቱ ለእግዚእነ     እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ “ሕዝብ ዘይነብር ውስተ ጽልመት ርእየ ብርሃን ዓቢየ ወለአለሂ ይነብሩ ውስተ ጽልመት ወጽላሎተ ሞት ብርሃን ሠረቀ ሎሙ”            በድንቁርናና በቀቢጸ ተስፋ ለነበሩ ሰዎች ፍጹም እውቀት ተሰጣቸው፤ ሞት ባመጣው ምስል ሞትን በመምሰል ለነበሩ ሰዎች ክርስቶስ ተወለደላቸው በሞተ ሥጋ በሞተ ነፍስ ለነበሩ ልጅነት ተሰጣቸው፤ በኃጢአት ለነበሩ ስርየት፤ በክህደት ለነበሩ ሃይማኖት ተሰጣቸው ኢሳ.ም 9፣2እግዚአብሔር የሁላችን አባት አዳምን በአርአያውና በመልኩ ከፈጠረው በኋላ ባረከው ሁሉንም እንዲገዛ እንዲነዳ ሥልጣን ሰጠው፤ በረከቱን፣ ሥልጣኑንና ሲሳዩን ከሰጠው በኋላ ፈጣሪውን የሚያስታውስበት ትዕዛዝ አዘዘው፡፡ ትዕዛዙም የፈጣሪና የፍጡር መለያ፣ የአዛዥና የታዛዥ ገደብ፣ ሰው ለሕግ መገዛት እንደሚገባው ለማስረዳት የተደረገ እንጂ የስስት ወይም የንፍገት አልነበረም፡፡ ይህንን ደግሞ አዳምም ሆነ ሔዋን ያውቁታል፤ በምግብ እጦት እንዳይቸገሩ ግን በገነት ያሉትን አትክልት እንዲበሉ ከውኃውም እንዲጠጡ ፈቅዶላቸዋል፡፡ሰው ግን ከፍጥረት አክብሮ አልቆ ያነገሠውን እግዚአብሔርን አስቀይሞ በተሳሳተ ምክር ተመርቶ አትብላ የተባለውን ዕፀበለስን ስለበላ ከፈጣሪውም ትዕዛዝ ስለወጣ በዚህ ምክንያት የሞት ፍርድ ተፈረደበት፡፡ ከኤዶም ገነት ተባረረ፣ ከአምላኩ ጋር ተጣላ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው አንድነት ግንኙነት ተቋረጠ “ወደ ወጣህበት ምድር እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ” ዘፍ 3፣19አለው ጥሮ ግሮ እንዲበላ የፈቀደለት የገነት ፍሬ ሳይሆን የተፈጠረባት ምድር ላይ እኛ የምንመገበውን ዕፅዋቱን፣ አዝዕርቱን፣ አትክልቱን፣ እንሰሳቱን ምግበ ሥጋ የሆነውን ሁሉ ነው፡፡እንደ መላእክት [...]
Tue, Jan 06, 2015
                               መልአኩን ልኮ አዳናቸው                        በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን                   በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታህሣሥ 19 ከከበሩት መላእክት አንዱ የሆነው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክበረ በዓል በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት በመዝሙር በጸሎት በምስጋና በቅዳሴ በዝክር ይከበራል ይታሰባል። የሚከበርበት ምክንያት ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሠለሥቱ ደቁቅን ከዕቶነ እሳት(ከነደደ እሳት) ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡           ቅዱስ ገብርኤል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው ብሏል ሉቃ 1፥20  ታላቁ ነብይ ሄኖክ ስለ ነገረ መላእክት በተናገረበት አንቀጽ እንዲህ ሲል መሰክሯል  ሄኖክ 6-710፥14 እያለ የመልአኩን ክብር ተናግሯል         ገብርኤል የሚለው ቃል የሁለት ቃለትውህድ ነው እነዚህም ገብር እና ኤል ትርጉምም የአምላክ አገልጋይ /የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል የአምላክ አገልጋይ ማለት ነው። ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን መላእክትን ”ንቁም በበእላዌነ እስከ ንረክቦ ላምላክነ ” አምላካችንን ፈጣሪያችንን እስከምናውቅ ድረስ ባለንበት በተረዳንበት ነገር ጸንትን እንቁም በማለት ያጽናና ያረጋጋበተወዳጁመልአክበቅዱስ ሚካኤል መሪነትየሰው ልጆች ጠላት የሆነውን ዲያብሎስን ተዋግተው ድል እንዲያደርጉ ወደ ጥልቁ እንዲጣል  አድርጓል (አክሲማሮስ ገጽ.35) ራእ12፥7 ነቢዩ ኢሳይያስ በሰማያት የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ሲጽፍልን “አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ  አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ፡ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደረጋለሁ፤… በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምደር ጥልቅም ትወርዳለህ”(ኢሳ.1416)በማለት ገለጠልን፡፡ ወደ ምድር የጣሉት በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል መሪነት እነ ቅዱስ ገብርኤል ነበሩ፡፡                ቅዱስ ገብርኤል በብሉይ ኪዳን በቅድስና ሕይወት ለተጋውና በገዢዎች ዘንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ያደረበት ሰው(ዳን.5፡11)ተብሎ ለተመሰገነው ለነቢዩ ዳንኤል ማስተዋልንና ጥበብን የሰጠ መልአክ ነበር፡፡ ለዚህ ነቢይ እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጆችን ከሰይጣንና ከሞት ባርነት ነጻ ሊያወጣቸው ሰው እንደሚሆንና ሰማይንና ምድርን አሳልፎ በቅዱሳን ላይ ነግሦ እንደሚኖር በምሳሌ ገልጾ ያስተማረው መልአክ ነው፡፡(ዳን.9፡21-22) አሁንም ነቢዩ ዳዊት “አቤቱ እርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብሰውብፁዕነው፡፡በልቅሶሸለቆ በወሰንኸቸውስፍራየሕግመምህርበረከትንይሰጣልና፡፡”(መዝ.83፡5-6)እንዳለውናቸው፡፡         ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን ይሆኑ ዘንድ ለተጠሩት መንፈሳዊ እውቀቱን የሚያካፍላቸው መልአክ ብቻ አይደለም፤ ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡ የፋርስ ንጉሥ የነበረው ናብከደነፆር እግዚአብሔር አምላክ ምድሪቱን ሁሉ ሲያስገዛለት በትዕቢት ተሞልቶ “በኃይሌ  አደርጋለሁ፣ በማስተዋል ጥበቤም  የአሕዛብን ድንበሮች አርቃለሁ፣ ሀብታቸውንም እዘርፋለሁ፣ የሚቀመጡባቸውንም ከተሞች አናውጣለሁ፣ በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰበስባለሁ፣ እንደ ተተወ እንቁላልም አወስዳቸዋለሁ፤ከእኔም የሚያመልጥ የለም የሚቃወመኝም የለም፡፡”(ኢሳ.10፡13-14) ብሎ በመታበይ የወርቅ ጣዖትን አሠርቶ ዱራ(አዱራን) በሚባል ስፍራ ላይ አቆመው፡፡ በግዛቱ በልዩ ልዩ የሥልጣን እርከን ላይ ያሉትን ሹማምንቱንና ገዢዎችን ሰበሰባቸው፤ “የመለከትና የእንቢልታ የመሰንቆና የክራር የበገናና የዋሽንትን የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ወድቃችሁ ንጉሥ ናብከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል ስገዱ፡፡ ወድቆም ለማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣል” ብሎ አዋጅ አስነገረ፡፡ ይህን አዋጅ የሰሙ የንጉሥ ሹማምንት ሁሉ የመለከቱና የእንቢልታው እንዲህም የዘፈን ድምፅ በተሰማ ጊዜ ተደፍተው ለወርቁ ምስል ሰገዱ፡፡        በባቢሎን አውራጃዎች ላይ የተሾሙ አዛርያ(ሲድራቅ)፣ አናንያና(ሚሳቅ) ሚሳኤል(አብደናጎ) ግን ንጉሥ ላቆመው ምስል አልሰገዱም፡፡ ነገር ሠሪዎችም ይህንን ወሬ ለንጉሥ ነገሩት፤ ንጉሥም እጅግ ተቆጥቶ ወደ እርሱ አስጠራቸው፡፡ እርሱ ላቆመው ለወርቅ ምስል ያልሰገዱ እንደሆነ እጅና እግራቸውን ታስረው ወደ እቶን እሳቱ እንደሚጣሉ አስጠነቀቃቸው፡፡ ሠልስቱ ደቂቅ ግን  “ናብከደነፆር ሆይ! በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አንፈልግም፡፡ ንጉሥ ሆይ! እኛ የምናመልከው አምላክ በሰማይ አለ፣ ከሚነደውም ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፤ ንጉሥ ሆይ! ይህም ባይሆን አማልክትህን አንዳናመልክ፣ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ” ብለው መለሱለት፡፡ የንጉሥ ናብከደነፆር ቁጣ ከፊት ይልቅ እጅግ ነደደ እሳቱንም ሰባት እጥፍ እንዲያቀጣጥሉና እነዚህን ሦስት ብላቴኖች እጅና እግራቸውን አስረው ከእነ ማዕረግ ልብሳቸው ከእቶን እሳት ውስጥ እንዲጨምሩአቸው ትእዛዝን አስተላለፈ፡፡ ትእዛዙ አስቸኳይ ነበርና እነርሱን ወደ እሳቱ የጣሏቸውም ኃያላን በእሳቱ ወላፈን ተገርፈው ሞቱ፡፡ እንዲህ ሲሆን ሳለ ግን ሠልስቱ ደቂቅ ወደ አምላካቸው “በፍጹም ልባችን እናምንሃለን፣ እንፈራሃለን፣ አታሳፍረን እንጂ ገጸ ረድኤትህንም እንፈልጋለን፡፡” እያሉ ይጸልዩ ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ጸሎታቸውን ተቀበለ፤ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልንም ከመጣባቸው መከራ ይታደጋቸው ዘንድ ላከው፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም እስራታቸውን ፈታ፤ እሳቱን እንደ ውኃ አቀዘቀዘው፡፡ ሠልስቱ ደቂቅም መልአኩን ልኮ ከዚህ እቶን እሳት ያዳናቸውን አምላክ “የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ስምህም ለዘለዓለም የተመሰገነና የከበረ ነው” በማለት አመሰገኑት፡፡  ንጉሥ ናብከደነፆርም ሠልስቱ ደቂቅ እሳቱ አንዳች ጉዳት ሳያደርስባቸው በእሳት ውስጥ ሲመላለሱ ከእነርሱ ጋር የሰው መልክ ያለው ነገር ግን አምላክን የሚመስል መልአክ ተመለከተ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሊቀ ካህናቱን ቀያፋን ፊቱን ጸፍቶ አፉን ከፍቶ “ሕዝቡ ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለሕዝቡ ይሞት ዘንድ እንዲሻለን አታስቡምን”(ዮሐ.11፡49) ብሎ እንዳናገረው እንዲሁ ናብከደነፆርንም “እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎችን በዚያ አያለሁ ምንም የነካቸው የለም፤የአራተኛውም መልክ የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል” ብሎ እንዲናገር አደረገው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅን መልክ ያለው ያለው በኋላም መልአክ ብሎ የተናገረለት ቅዱስ ገብርኤልን ነበር፡፡ እርሱ ስለመሆኑ ለነቢዩ ዳንኤል በተገለጠበት ግርማ ማረጋገጥ እንችላለን፡፡                     ናብከደነፆርም ወደ እሳቱ እቶን በመቅረብ እነዚህ ብላቴኖችን “እናንተ የልዑል አምላክ ባሮች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ኑ ውጡ ብሎ ተናገራቸው፡፡” እነርሱም ከእሳቱ ወጡ ሹማምንቱና መኳንንቱ፣ አማካሪዎችና የአገር ገዢዎች ሁሉ እሳቱ በእነዚህ ብላቴኖች ላይ አንዳች አቅም እንዳልነበረው፣ ከጠጉራቸው ቅንጣት አንዱን እንኳ እንዳላቃጠለው፣ ሰናፊናቸውም እንዳልተለወጠ፣ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው ተመለከቱ፡፡ ንጉሥ ናብከደነፆርም መልአኩን ልኮ ያዳናቸውን የእነዚህን ቅዱሳንን አምላክ አመሰገነ፡፡ በእነርሱ አምላክ ላይም የስድብን ቃል የሚናገር ሰው እንደሚገደልና ቤቱም የጉድፍ መጣያ እንዲሆን አዋጅ አስነገረ፡፡ አዛርያ አናንያ ሚሳኤልም በንጉሡና በሹማምነቱ ዘንድ ሞገስ አገኙ በክብርም ከፍ ከፍ አሉ፡፡(ዳን.3 በሙሉ)  ሊቀ ነቢያት ሙሴ> እና ብሎ የሰራዊት ጌታ ቅዱሳን መአእክትን እንዳከበራቸው አስተምሮናል           ቅዱስ  ገብርኤል በአማላጅነቱ በጸሎቱ ለታመኑበት ፈጥኖ የሚደርስ በብለይ እና በሐዲስ ኪዳን በልዪልዩ ተልኮዎቹ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ፈቃድ በመፈጸም የጸና ሰለሆነ ጥበብ በመግለጽ በማጽናት በማብሰር ከመከራ በማዳን ከእሳት ወላፈን በመታደግ ከአንበሳ መንጋጋ በማትረፍ እና ትዕቢተኞችን በመቅጣት በመገሰጽ እውነተኛ ታዳጊ መልአክ መሆኑን አስመስክሯል ።ሰለስቱ ደቂቅን በሚያሰደንቀው ትንብልናው እንደታደጋቸው እንደተራዳቸው ዛሬም በጸሎቱ ለሚታመኑ ዝክሩን ለሚያደርጉ ድረሳኑን የሚደግሙትን በጸሎት በመዝሙር በቅዳሴ በልዮ ልዮ መንፈሳዊ ክብረ በዓሉን ብናናክበር አማላጅነቱን የጸጠውን ጸጋ ብንመሰክር በበደላችን ምክንያት ከተግባረ ጽድቅ ለተሰደድን ስደተኞች ከባሕረ እሳት ለሰጠምን ኃጥያተኞች የምናመልከው ያባቶቻችን አምላክ ለመልአኩን ልኮ የእሳቱን ባሕር እንዲያሻግረን የሊቀ መላእክትየቅዱስ ገብርኤል አማላጅነቱ የሰለሰቱ ደቂቅ በረከታቸው  ይደርብን                                     ምንጭ   ደርሳነ  ገብርኤል                                          [...]
Thu, Dec 27, 2012
   ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት ይመለከታታልን ?  ክፍል 6     ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት ይመለከታታልን? ከዚህ ቀደም ባቀረብናችው ጽሁፎች  እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም  የጥንተ አብሶ ፍዳ እንደ ማይመለከታት ቅዱሳን አባቶቻችን የተናገሩትን መመልከት ጀምረን ነበር በዚህ ጽሁፋችንም ቀጣዩን ክፍል እንመለከታለን  አምላካችን ልዑል እ ግዚአብሔር የእናቱን በረከት ረድኤት ያሳድርብን አሜን   ቅዱስ  ኤራቅሊስ  በሃይማኖተ  አበው ምዕራፍ  48 ቁጥር 31  ስለ እመቤታችን ንጽህና ሲመሰክር እንዲህ ይላል       « ኢያእመረ እስመ ዘተፈጥረት እምነ ጽቡር ጽሩይ ትከውን  መቅደሶ ለእግዚአብሔር »ትርጉም « የእግዚአብሔር መቅደሱ ማደርያው ትሆነው ዘንድ ከንጹህ አፈር (ዘር)የተፈጠረች  መሆኗን አላወቀም  » ታላቁ የቤተክርስትያን አባት ቅዱስ ኤራቅሊስ  ይህንን ኃይለ ቃል የተናገረው አረጋዊ ካህን ዮሴፍ ለእመቤታቸን አገልጋይ ሆኖ የታጨለትን ምሥጢር በተረጎመበት ክፍል ነው  ።በእርግጥ አረጋዊ ዮሴፍ ለእመቤታችን ለምን እንደታጨ አላወቀም ነበር እርሷም ትንቢት የተነገረላት ሱባዔ የተቆጠረላት አምላክን በድንግልና ጽንሳ በድንግልና የምትወልድ ከመርገመ አዳም  ከመረገመ ሔዋን የተለየች መሆኗን አላወቀም ነበር። ነገሮችን መረዳት የጀመረው መልአኩ ካረጋጋው በኃላ የተለያዩ ምልክቶችን አይቶ ነው ።ሊቁም ይህንን ሲያስረዳ « የእግዚአብሔር መቅደሱ ትሆነው ዘንድ ከንጹህ አፈር የተፈጠረች መሆኗን አላወቀም «          ይህም አገላለጽ ወላዲተ አምላክ ስትፈጠር ጀምሮ ንጽህት ቅድስት መሆኗን ያስርዳል ዮሴፍ ማንነቷን ከማወቁ በፊት እንደማናቸውም አንስት ከአዳማዊ እዳ በደል ያልተለየች ሴት መስላው ነበር ሁሉን የተረዳው ቆይቶ ነው ድንግል ማርያም ግን ሊቁ እንደተናገረው ተፈጠሮዋን በተመለከተ « ከንጹህ አፈር « በማለት ንጽሐ ጠባይዋ ያላደፈባት ያልጎደፈባት ገና በማህጸን አጥንት  ሰክቶ ሲፈጥራት በንጸህና የጠበቃት ስለሆነች ከንጹህ አፈር የፈጠራት በማለት ተናገረ ። ድንግል የአምላካችን አማናዊት መቅደስ ናት  እንደ ደንግል ማርያም የእግዚአብሔር ማደርያ የሆነ ማንም የለም በሌሎቹ ሁሉ ቢያድር በጸጋ [...]
Mon, Oct 29, 2012