የእግዚአብሔር ባህሪያት
፩ መንፈስነት
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፥17 ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ።
፪ ዘላለማዊነት
፫ ሁሉን ቻይነት
፬ አለመለወጥ
ትንቢተ ሚልክያ – ምዕራፍ 3:6፤ እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፤ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም።
፭ ምሉእነት
ትንቢተ ኤርምያስ 23:23 እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለሁም።
፮ መለኮታዊ ጥበቃ
መዝሙር 138 ፥7 በመከራ መካከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ሕያው ታደርገኛለህ፤ በጠላቶቼ ቍጣ ላይ እጆቼን ትዘረጋለህ፥ ቀኝህም ታድነኛለች።
ማቴ 10፥30 የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል። ዘፍ ፴፯፥፲፰ ኢዩ ፩፥፲፪
፯ አዋቂነቱና ጥበቡ
ወደ ሮሜ ሰዎች 11:33 የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም።
፰ ቅዱስነት
፱ ደግነት
መዝሙረ ዳዊት
86፥15 አቤቱ፥ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፤ መዓትህ የራቀ ምሕረትህም እውነትህም የበዛ፤
145፥8 እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሓሪ ነው፥ ከቍጣ የራቀ፥ ምሕረቱም ብዙ ነው
፲ የማንንም እርዳታ አለመፈለጉ
ወደ ሮሜ ሰዎች 11 : 34 – 36
የጌታን ልብ ያወቀው ማን ነው፧
ወይስ አማካሪው ማን ነበር፧ ወይስ ብድራቱን ይመልስ ዘንድ ለእርሱ አስቀድሞ የሰጠው ማን ነው፧
ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።