Exam1

  1. ከሚካተሉት ስለ መላእክት ትክክል የሆነውን ምረጥ

ሀ/ መላእክት ከእሳትና ከነፋስ እንዲሁም ከብርሃን ተፈጥረዋል

ለ/ መላእክት ቁጥር ስፍር የላቸውም

ሐ/ መላእክት ፻ ነገድ ፲ ከተማ ይከፈላሉ

መ/ መላእክት በኢዮር በራማ እና ኤረር ሶስቱ የታችኛው የሰማይ ክፍሎች ይኖራሉ

 

  1. የሚከተሉትን የእግዚአብሔር ስሞች ያለና የሚኖር የሚል ትርጉም ያለው የትኛው ነው

ሀ/ ኤል  ለ/ ኤልሻዳይ  ሐ/ ያኸቡየ  መ/ አዶናይ ሠ/ እግዚአብሔር

 

  1. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከምትመራባቸው ሶስቱ መሰረታዊ የሕግ ወይም የትምሕርት

ዘርፎች ቅብብል ፣ ርክክብ ወይም ውርስ ማለት የትኛው ነው

ሀ/ ዶግማ  ለ/ ቀኖና  ሐ/ ትውፊት

 

  1. የሰው ልጅ እግዚአብሔርን በምን ይመስለዋል
    ሀ/ በዕውቀት ለ/ በአገዛዝ ሐ/ በመልክ መ/ በነፍስ
  2. ከሚከተሉት የትኛው ስሕተት ነው
    ሀ/ ሃይማኖት እባቡን ለመርገጥ ጊንጡን ለመጨበጥ መርዝን ለመጨለጥ

ዲያቢሎስን ድል ለመንሳት አጋነንትን ለመግዛት ስልጣን ትሰጣለች
ለ/ ሃይማኖት የሚገለጠው በምግባር ነው
ሐ/ ምግባር ያለ ሃይማኖት ሊሰራ አይችልም
መ/ ሃይማኖት የፍጡር ሕሊና መርምሮ የማይፈጽማት ምስጢር ናት

  1. የሃይማኖት ጥቅም የሆነው
    ሀ/ ሰው ተፈጥሮውን ምንነቱን አቅሙን ይሚያውቅበት የሚረዳበት ነው
    ለ/ ሰው ከሞተ ነፍስ ከደዌ ሥጋ የሚድንበት ነው
    ሐ/ ሃይማኖት በትንሣኤ ሙታን ማመን ነው
    መ/ሰው እየሱስ ክርስቶስ በምድር የሰራውን ከዛም የሚበልጥ መስራት ታስችላለች
    ሠ/ ሃይማኖት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚይያስረግጥ

የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው

  1. በስነ ፍጥረት መሰረት ቅደም ተከተሉን አስተካክል

አሳ ፣ ሳር ፣ በግ ፣ መሬት

  1. በስነ ፍጥረት መሰረት ቅደም ተከተሉን አስተካክል

ፀሃይ ፣ ጠፈር ፣ ሰማይ ፣ ብርሃን

  1. ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊው በውዳሴ ማርያም እመቤታችንን

ከመሰለበት የስነ ፍጥረት ዕለት አንዱ ማን ነው

  • የእግዚአብሔር ባሕሪያት ተምረናል። 6 የእግዚአብሔር ባሕሪያት ጻፍ
  • የእግዚአብሔር መኖር የሚታወቅባቸው 5 ነገሮች ተምረናል። 4ቱን ጻፍ