የሃይማኖት ትምህርት ፈተና

 

  1. የሥላሴ ሦስትነት እና አንድነት በምን በምን ነው
  2. የሥላሴ ሦስትነትና አንድነት የሚያሰረዳ ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጥቀስ
  3. የሥላሴ ሦስትነትና አንድነት የሚያሰረዳ ምሳሌ ጥቀስ
  4. ስለ ምሥጢረ ሥጋዌ ሁለት ማስረጃ ጥቀስ
  5. ስለ ምሥጢረ ሥጋዌ ሁለት ምሳሌ ጥቀስ
  6. በምሥጢረ ሥጋዌ ትምህርት የቱሳኤ እና ቡአዴ ልዩነት አስረዳ ከተዋሕዶ አንጻር
  7. በምሥጢረ ሥጋዌ ትምህርት የኅድረት እና ፍልጠት ልዩነት አስረዳ ከተዋሕዶ አንጻር
  8. የጥምቀትን አስፈላጊነት አብራራ
  9. ለምን ጥምቀት በ ጌታ በ፴ ዓመቱ እንደተጠመቀ መጽሐፍ ይነግረናል እኛ ለምን በ፵ እና ፹ ቀናችን እንጠመቃለን
  10. ምሥጢረ ጥምቀትን የምንፈጽምባቸው ፪ ጥቅሞች ግለጽ
  11. ስለ ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን የሚያሰረዳ ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጥቀስ
  12. ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም የተነገሩ ሁለት ምሳሌዎች አስረዳ
  13. ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም የተነገሩ ሁለት ትንቢቶችን ግለጽ
  14. የቅዱሳንን አማላጅነት አካለ ሥጋ ና በአካለ ነፍስ አማላጅነት የሚያስረዳ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ጥቀስ
  15. የእግዚአብሔርና የቅዱሳን ቅድስና ልዩነት ምንድን ነው:: ቅዱሳን የምንላቸውስ እነማን ናቸው
  16. የነገረ ቅዱሳን እና የነገረ ድኅነት ትምህርት ልዩነታቸውና አንድነታቸው ምንድነው
  17. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ጥንተ አብሶ የለባትም ብላ ታምናለች። ይህ ማለት ምን ማለት ነው። ይህንን መጽሐፍ ቅዱስ ወይም አዋልድ መጽሐፍት ተጠቅመህ አስረዳ።
  18. አንድ ሰው ለመዳን ምን ማድረግ ይኖርበታል ከቤተ ክርስቲያን አስተምሮ አንጻር አስረዳ
  19. ስግደት ስንት አይነት ነው? ስግደት ለማን ይገባል? መጽሐፍ ቅዱስ ጠቅሰህ አስረዳ
  20. ከዚህ ኮርስ አዲስ ነገር ተማርኩ የምትለውን ሁለት ነጥብ ግለጽ? ስለ ኮርሱ አጠቃላይ አስተያየት ፣ ሊሻሻል የሚገቡ ጉዳዮች ዘርዝር