Quiz4

  1. ከሚከተሉት ስለ ምሥጢረ ሥጋዌ ትክክል የሆነውየሆነው የቱ ነው

ሀ/ ሥጋዌ ማለት ሥጋ ሆነ ሥጋ ለበሰ ጎላ ገዘፈ ማለት ነው

ለ/ ምሥጢረ ሥጋዌ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ በተለየ አካሉ ሰው የሆነበት ምሥጢር ነው

ሐ/ ቅድመ ዓለም አብ ያለ እናት የተወለደ እግዚአብሔር ወልድ ከመቤታችን መውለዱ

መ/ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረ ቃል ከሰማያት ወርዶ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሳ ነፍስ መንሳቱ

ሠ/ በቃልነቱ ከዊን ከመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሳው ሥጋ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባህሪ አንድ ባህሪ መሆኑ

ረ/ አምላክ ሰው ፤ ሰው አምላክ መሆኑ

ሰ/ ሥጋ በተዋሕዶተ ቃል የባሕርይ አምላክ ተባለ ለአብ የባሕርይ ልጅ ሆነ

 

  1. ስለ ምሥጢረ ሥጋዌ ሁለት ማስረጃ ጥቀስ

 

  1. ስለ ምሥጢረ ሥጋዌ ሁለት ምሳሌ ጥቀስ

 

 

4. አዛምድ

 

1. ቱሳኤ

2. ቡአዴ

3. ቅዱስ ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮት

4. ተዋሕዶ

5. ኅድረት

6. ፍልጠት

7. ውላጤ

8. ቅዱስ ዲዮስቆሮስ

 

ሀ/ መዶሻ ወይም መጥረቢያ

ለ/ ከተዋሕዶ በኋላ የሚመጣ መለያየት

ሐ/ የቃና ዘገሊላ ወይን ወይም የሎጥ ሚስት

መ/ ውሃ በማድጋ ወይም ሰይፍ በሰገባው

ሠ/ ቃል ሥጋ ሆነ ወኅደረ ላዕሌነ

ረ/ መቀላቀል መደባለቅ

ሰ/ አካላዊ ቃል ሰው ቢሆን ሥጋ ቢለብስ ምንታዌ የሌለበት አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው እንጂ በምንም በምን ሁለት አይባልም
ሸ/ ክርስቶስ ሕማም ሞት የሌለበት ፍጹም አምላክ ሲሆን ሕማም ሞት ያለበት ፍጹም ሰው ቢሆንም ያለመለያየት አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው